"አፍሪካውያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሊከሰት ለሚችል የከፋ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው"

ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የጌታው የቢልጌትስ ትዕዛዝ ተቀብሎ  ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሐኖም   "አፍሪካውያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሊከሰት ለሚችል የከፋ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው" እያለን ነው።

ለጥቁር ሕዝቦች የተፈጠረ ቫይረስ ሲመጣ ዓለም ጥቁሩን እንዴት እንደምታገለው ለመገመት አያዳግትም ፤ “የሰውን ልጅ ለማዳን” በሚል ሰበብ መላው አፍሪቃ ላይ አርከፍክፈው ሰውን ሁሉ እንደ ቆሻሻ ያቃጥሉታል። ዲያብሎሳዊ ፍላጎታቸውና አላማቸው ይህ ነው።  

የEthiopian Broadcasting Corporation ምስል


አፍሪካውያን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ ሊከሰት ለሚችል የከፋ ሁኔታ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሪክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም አሳሰቡ።



የዓለም ጤና ድርጅት በ33 የአፍሪካ አገራት ውስጥ 633 የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸውንና እስካሁን 17 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ አድርጓል።

ቫይረሱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በፍጥነት የመዛመት ባህርይ እንዳለው የገለጹት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሪክተሩ፣ ይህ ቁጥር ዝቅተኛ መሆኑ አፍሪካውያንን ሊያዘናጋ አይገባም ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ አገራት 233 የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች መመዝገባቸውን፣ ሆኖም ግን አሁንም ያልተደረሰባቸው እና ሪፖርት ያልተደረጉ ታማሚዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ማናቸውም ዓይነት የሰዎች መሰባሰብ ሊቆም ይገባል፣ አፍሪካ ልትነቃ ይገባል በማለት በአጽንኦት አሳስቧል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ ጋምቢያ፣ ሞሪሽየስ እና ዛምቢያ የመጀመሪያ ታማሚዎች ማግኘታቸውን ይፋ አድርገዋል ብሏል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም በበኩላቸው ትላንት በሰጡት መግለጫ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ቁጥር ከ200 ሺህ በላይ መድረሱን እና ከስምንት ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን ገልጸዋል።

በሽታውን ይበልጥ ለመከላከል አገራት የበሽታው ምልክት ያለባቸውን ሰዎች መለየት፣ መመርመር፣ ማስታመም እና ሌሎች ታማሚዎች መኖር አለመኖራቸውን መከታተል መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

በርካታ አገራት ከድርጅታቸው የሚወጡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑንም አመልክተዋል።

ምንጭ:- የዓለም ጤና ድርጅት

Post a Comment

0 Comments