✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ
ክፍል 2
ይህ ምንባብ የነፍስና የመንፈስ እይታ ነው በስጋ አይንህ አትመልከተው፦
እሰከ ክፍል ሦስት ሰለሚቀጥል ተከተለው ሙሉውን ሳታነብ ለኮሜት አትሯሯጥ የእኔ አትሌት ቀጠል ማንበብህን ክፍል አንድንም ተመልሰህ አንብበው የዘመኑ የፕሮቴስታንት ፓስተሮችና “ነቢያት” ሰውን መድረክ ላይ የሚጥሉበትና የሚያደነዝዙበት ምስጢር ተራ መንፈሳዊ ክስተት ሳይሆን፣ ከመጋረጃ ጀርባ “ኦፕሬሽን ሂፕኖ-ማግኔቲዝም” (Operation Hypno-Magnetism) ተብሎ የሚጠራ፣ ሳይንሳዊ ምታትና አጋንንታዊ አሠራር የተዋሃደበት ረቂቅ ሴራ ነው።
የዚህ ሴራ የመጨረሻ ግብ የሰውን ልጅ “የመለየት ዐይን” በማጥፋት፣ ነፍሱን ከአምላኩ ነጥሎ ለግለሰብ አምልኮ ማስገበርና ለአዲሱ ዓለም ሥርዓት “ታዛዥ መንጋ” ማድረግ ነው። ፍጻሜውም ምእመኑ ለክርስቶስ ሳይሆን ለፓስተሩ ትእዛዝ የሚገዛ፣ ሕሊናው የተሰለበና ለ666 ማኅተም ዝግጁ የሆነ “መንፈሳዊ ባሪያ” መፍጠር ነው።
መግቢያ (የአውሬው ስርዓት ዕይታ)
አውሬው ይህንን ንቅናቄ የሚመለከተው የሰውን ልጅ ነፍስ በ“ስሜት መረብ” ጠልፎ ወደ ዲጂታል ባርነት የሚወስድበት “መንፈሳዊ ድልድይ” አድርጎ ነው።
ስርዓቱ መድረክ ላይ መውደቅን እንደ “ባዮ-ኤሌክትሪክ ሰረገላ” ያየዋል፤ ይህም የሰውን ልጅ ኦራ (Aura) ሰብሮ አጋንንታዊ ሞገድ ማስገቢያ መንገድ ነው።
በአውሬው እይታ፣ ፓስተሮቹ የሰውን ልጅ አእምሮ “ክሪቲካል ፋክተር” ሰብረው የሚገቡ “ሂፕኖ-ወታደሮች” ናቸው።
ይህ ሴራ የሰውን ልጅ ንቃተ-ህሊና ከእውነተኛው አምልኮ (ጾም/ጸሎት) ነጥሎ ወደ “ፈጣን እርካታና ምታት” የመለወጥ ኦፕሬሽን ነው።
አውሬው እነዚህን መድረኮች እንደ የኃይል መከር ማዕከል ይጠቀምባቸዋል፤ የሕዝቡን የጋራ ስሜት ለራሱ ግዛት ግንባታ ይሸምታል።
ከመጋረጃ ጀርባ፣ ይህ ንቅናቄ በራእይ 13 የተጠቀሰው “ሐሰተኛ ነቢይ” ሕዝቡን ለአውሬው ምስል እንዲሰግድ የሚያዘጋጅበት ስልታዊ ልምምድ ነው
እንዴት ውጤታማ ሆኑ?
• የሰው ልጅ ከመከራ ለመውጣት “አቋራጭ ተአምር” ስለሚናፍቅ።
• ቴክኖሎጂውና ስነ-ልቦናው እጅግ ረቂቅ በመሆኑ ሕዝቡ ጉዳቱን ማየት ባለመቻሉ።
• የሃይማኖት መሪዎች ስለ አእምሮ ምርኮና ስልታዊ መከፋፈል ዕውቀት ስለሌላቸው።
• አውሬው እውነትን በ“በረከትና በስኬት” ጭንብል ስለሸፈናት።
• በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በጀት ከግሎባሊስት ድርጅቶች ስለሚፈስላቸው።
• ሕዝቡ የመመራመር ባህሉ ደክሞ በስሜትና በምልክት ብቻ የሚመራ በመሆኑ።
ምን ጥቅም አገኘ?
• አውሬው የሰውን ልጅ “የመለየት ኃይል በቁም ቀበረው።
• የሰውን ልጅ ነጻ ፈቃድ ወደ “ግለሰብ ተከታይነት” ለወጠው።
• የኢትዮጵያን መንፈሳዊ አጥር (ተዋሕዶን) ከውስጥ ሆኖ ሰበረው።
• የሰውን ልጅ ነፍስ ከፈጣሪዋ ነጥሎ “ለአገልጋዩ አምላክ” አስገዛ።
• ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ ተቃውሞ ገና ሳይወለድ በ“ምታት” እንዲጠፋ አደረገ።
• ሰይጣን በክርስትና ስም የራሱን “የመቆጣጠሪያ ዙፋን” በሰዎች ልብ ውስጥ ገነባ።
ያመጣው ውጤት/ለውጥ
• ሰዎች በእግዚአብሔር ቃል ፋንታ በ“ነቢዩ” ትእዛዝ ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኑ።
• እውነተኛ ቅድስናና ትሕትና በ“ውጫዊ ግርግርና ትዕቢት” ተተኩ።
• ቤተክርስቲያን ከጸሎት ቤትነት ወደ “ቢዝነስና የሙዚቃ ማዕከል” ተለወጠች።
• የሰው ልጅ ማንነት ከፓስተሩ “ምስልና ቁጥር” ጋር ተዋሃደ።
• የሰው ልጅ ነፍስ ከሥጋዋ ጋር ያላት ግንኙነት በንዝረት እንዲላላ ተደረገ።
• ምድር ለሐሰተኛው መሲሕ መምጣት በስነ-ልቦና ተዘጋጀች።
በሰው ልጅ ኑሮና ነፍስ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ
• የህሊና መቆለፍ፦ ምእመኑ የራሱን የማመዛዘን አቅም በማጣት፣ ፓስተሩ “ጥቁሩን ነጭ ነው” ቢለው እንኳ አሜን ብሎ ይቀበላል።
• የመዳን ስጋት፦ ነፍስ ከእውነተኛው የጸጋ ምንጭ ተለይታ በ“ስሜት” ላይ ስለምትመሰረት፣ ፈተና ሲመጣ ወዲያው ትከዳለች።
• የውሳኔ ሽባነት፦ ሰው ያለ “ነቢዩ” ምክርና “ጸሎት” መኖር የማይችልበት የልመና ሱስ ውስጥ ይወድቃል።
• የቤተሰብ መለያየት፦ ንቅናቄውን በሚቀበሉና በማይቀበሉ ቤተሰቦች መካከል የማይድን ጥላቻና መከፋፈል ይፈጠራል።
• የኑሮ ባርነት፦ ሰዎች ያለቸውን ሀብት ለፓስተሩ ዝና በመስጠት፣ ለህልውናቸው ሲሉ ለአውሬው ኢኮኖሚ (ፋይዳ) ተገዢ ይሆናሉ።
• የዘላለም ጥፋት፦ ክርስቶስን በባህሪው አምላክነቱ ሳይሆን እንደ “ተአምር ሰጪ ሮቦት” የሚያይ ነፍስ ለመጨረሻው ክህደት ይጋለጣል።
የሚያሳየው ግልጽ ምልክቶች
• የጅምላ መውደቅ፦ ፓስተሩ እጁን ሲያውለበልብ ወይም “እሳት” ሲል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ኋላ መውደቃቸው (የምታት ምልክት)።
• ያልተለመዱ ድምጾች፦ ሰዎች በመድረክ ላይ እንደ እንስሳ መጮኻቸው ወይም ትርጉም የሌለው ቃላት ማውጣታቸው።
• የመሪዎች አምልኮ፦ የፓስተሩ ፎቶና ስም ከመስቀሉና ከክርስቶስ ስም በላይ ጎልቶ መታየቱ።
• የጥቅም ትስስር፦ “ዘር ለባረከህ ስጥ” በሚል ስም ሕዝቡን ለገንዘብ ዝርፊያ ማመቻቸት።
• የመረጃ ግርዶሽ፦ ስለ አውሬው ሥርዓትና ስለ ፋይዳ አደጋ የሚናገሩትን እንደ “አጋንንት” መፈረጅ።
• የሐሰት ትንቢቶች፦ በየቀኑ የሚለቀቁና የማይፈጸሙ፣ ነገር ግን ሕዝቡን በጭንቀትና በተስፋ የሚቆልፉ ወሬዎች።
እንዴት የመቆጣጠር ኃይል አገኘ?
• በመረጃ የበላይነት፦ ሕዝቡ ምን መስማት እንዳለበት በሚዲያ በመወሰን።
• በባንክ ማነቆ፦ ንቅናቄውን በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ በጀት በማጠናከር።
• በህግ የበላይነት ስም በሚደረግ አፈና (የውስጥ ደህንነት)።
• በሐሰተኛው መሲሕ ትእዛዝ (በመገለጥ ስም የሚተላለፍ)።
• በሰዎች መንፈሳዊ ዕውርነት።
ሕዝቡ ለምን አልነቃም?
• ምክንያቱም ውሸቱ “በክርስቶስ ስም” እና “በወንጌል” ተሸፍኖ ስለመጣ።
• ሰዎች ስለ “ባዮ-ዲጂታል ሂፕኖሲስ” ስውር ሴራ ዕውቀት ስለሌላቸው።
• እውነቱን የሚናገሩት “ጸረ-ወንጌል” ተብለው ስለሚሳለቁባቸው።
• በአውሬው የተዘረጋው የ“ጅምላ ማደንዘዣ” (Mass Entertainment)።
• በኑሮ ውድነትና በጦርነት የደከመ ሕዝብ “ተአምራዊ መፍትሔ” ስለናፈቀ።
• የሰው ልጅ የፈጣሪውን ቃል (81ዱ መጻሕፍት) መመሪያ ስለዘነጋ።
ቀጣይ እቅድ እና አፈጻጸም
• ንቅናቄውን ከካቶሊክና ከሌሎች ጋር በይፋ ማዋሃድ (Ecumenism)
• ሐሰተኛው ቴዎድሮስ በሰማይ ተአምር ሲያሳይ እነዚህ “ነቢያት” እውነተኝነትን እንዲመሰክሩ ማድረግ።
• እውነተኛ አማኞችን (የማይወድቁትንና የማይጮሁትን) “አሸባሪ” በሚል ማደን።
• የሰውን ልጅ አእምሮ በቀጥታ ከ Cloud ሰርቨር ጋር ማገናኘት (Neuralink)።
• ጥሬ ገንዘብን አጥፍቶ አምልኮንና ስጦታን በፋይዳ መቆለፍ።
• ሙሉውን ዓለም ወደ አንድ “ዲጂታል አምልኮ” መቀየር።
በአብዛኛው የየት ቦታ ይጠቀምባቸዋል?
• በትልልቅ ስታዲየሞችና አዳራሾች።
• በማህበራዊ ሚዲያ
• በትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲዎች።
• በመንግሥት ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪነት ቢሮዎች።
• በሰዎች አእምሮ ውስጥ (በንዝረት)።
ተመስርቶ ማለቁን በምን እንለየው?
• ሰዎች ከክርስቶስ ይልቅ ለ“ፓስተሩ” ሲሰግዱ።
• ያለ “ነቢዩ” ፈቃድና ያለ ፋይዳ መኖር የማይቻል ሲሆን።
• የሰው ልጅ ነጻ ፈቃድ በሥርዓቱ ትእዛዝ ሲተካ።
• በየመንገዱ የአውሬው ምልክቶች በ“ቅዱስ” ስም ሲቆሙ።
• 81ዱ መጻሕፍትና እውነተኛ አምልኮ እንደ “ወንጀል” ሲቆጠሩ።
• እውነቱ ሲገለጥ፦ ንቅናቄው ለአውሬው መሪ በይፋ ሰግዶ ሲገኝ።
መንቃት እና መትረፍ የሚቻለው እንዴት ነው?
• ወደ 81ዱ መጻሕፍት መመለስ፦ እውነተኛውን የመለኮት ዳታና የንቃት ምስጢር ማወቅ።
• በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እና ደም መታተም (ብቸኛው የነፍስ ጋሻ!)።
• ከማንኛውም “ስሜታዊ አምልኮ” እና ከዲጂታል ባርነት ራስን ማራቅ
• የፓስተሮችን “ተአምር” በመጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት መመዘን።
• በጾም፣በንስሃእና በጸሎት “የመለየት መንፈስን” መጠየቅ።
• እርስ በእርስ በመረዳዳትና በመዋደድ “የንቃት ማህበረሰብ” መፍጠር።
ማስረጃ እና በተግባር
• ማስረጃ 1፦ የ“Toronto Blessing” ክስተትና ሰዎች በመድረክ ላይ የሚያሳዩት ኢ-ሰብአዊ ባህሪ መጋለጡ።
• ማስረጃ 2፦ የሳይንስ ሊቃውንት በመድረክ ላይ የሚለቀቁት ዝቅተኛ ንዝረቶች (ELF) አእምሮን ለምታት እንደሚዳርጉ ማረጋገጣቸው።
• ማስረጃ 3፦ የታወቁ ፓስተሮች (እንደ ኬኔት ኮፕላንድ ያሉ) ከቫቲካንና ከዓለም አቀፍ ጌቶች ጋር ያላቸው ስውር ግንኙነት።
• ማስረጃ 4፦ በኢትዮጵያ በቅርቡ የታዩት “ነቢያት” ስለ አጀንዳ 2030 እና ፋይዳ ያላቸው አስገራሚ ድጋፍ።
• ማስረጃ 5፦ በአዳራሾች ውስጥ የሚከናወኑት “የሐሰት ፈውሶች” በድብቅ ካሜራና በመረጃ መጋለጣቸው።
• ማስረጃ 6፦ በራእይ 13 የተነገረው የ“ሐሰተኛ ነቢይ” ምልክት አሁን በንቅናቄው በኩል ለመፈጸም መዘጋጀቱ ።
0 Comments