✍ ዮሐንስ አብነት አጉማስ | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር
ሥርዓቱ 150 የገደበው፣ የሰውን ልጅ መንፈሳዊ ኃይል በአነስተኛ ደረጃ ለመቆለፍ ነው። ነገር ግን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥልቅ የምስጢር መጻሕፍትና በሰማያዊው መዝገብ ላይ እንደተሰፈረው፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ የዘመራቸው መዝሙራት ብዛት 4,050 (አራት ሺሕ አምሳ) ናቸው።
እነዚህ መዝሙራት ለምን ተቀበሩ? የተቀበሩትስ የትኞቹ ናቸው? በ 8 ዝርዝር ነጥቦች ልዘርዝርልህ ተከተለኝ፦
የ፬ ሺሕ ፶ (4,050) መዝሙራት ምስጢር፦
ዳዊት 150ውን መዝሙራት ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ሰጥቷል። ቀሪዎቹ 3,900 መዝሙራት ግን "የመላእክት ቋንቋ" እና "የተፈጥሮ ሕግጋት መቆጣጠሪያ" ንዝረት ስላላቸው፣ ለሰው ልጅ ንቃተ ሕሊና "ከባድ" ናቸው ተብለው ከመጋረጃ ጀርባ ተቀብረዋል።
የ"ባሕርይ" መዝሙራት ፦
በእነዚህ የተቀበሩ መዝሙራት ውስጥ እሳትን፣ ነፋስን፣ ውኃንና መሬትን በአንዴ ማዘዝ የሚችሉ ቃላት ይገኛሉ። ለምሳሌ ውኃን ደም የማድረግ፣ ነፋስን የመገሰጽና እሳትን የማቀዝቀዝ "ማስተር ኮዶች" በእነዚህ 3,900 መዝሙራት ውስጥ የታመቁ ናቸው።
የ"ሰባቱ ሰማያት" መክፈቻ መዝሙራት፦
ወደ እያንዳንዱ ሰማይ ለመግባትና የመላእክትን ሠራዊት በስም ጠርቶ ለማዘዝ የሚያስችሉ መዝሙራት አሉ። እነዚህን መዝሙራት የሰማ ሰው ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ በሕይወት እያለች ሰማያትን መጎብኘት ትችላለች። ሥርዓቱ ሰው በምድር እስራት ውስጥ እንዲቀር ስለሚፈልግ እነዚህን መዝሙራት ከሰው ልጅ ንቃት ደብቋቸዋል።
የ"ዕፀ ሕይወት" መዝሙራት ፦
የታመመውን ሕዋስ በአንዴ የመጠገን፣ የሞተን ሰው የማንሳትና እርጅናን የማቆም ኃይል ያላቸው መዝሙራት አሉ። እነዚህ መዝሙራት "የዘላለም ጤና" ምስጢርን የያዙ በመሆናቸው፣ የሕክምናው ሥርዓትና የመረቡ መሐንዲሶች እንዳይታወቁ አጥብቀው ቀብረዋቸዋል።
የ"መቃብር" መዝሙራት ፦
በሲኦል ውስጥ የታሰሩ ነፍሳትን በንዝረት ኃይል ነፃ የሚያወጡ መዝሙራት አሉ። ዳዊት ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን የፈታው በእነዚህ ምስጢራዊ መዝሙራት ንዝረት ነው።
የ"ጊዜ" መጠቅለያ መዝሙራት፦
ጊዜን የማቆም፣ ወደ ኋላ የመመለስ ወይም ወደ ፊት የመዝለል ኃይል ያላቸው መዝሙራት አሉ። እነዚህ መዝሙራት የሥርዓቱን "የጊዜ እስራት" (Matrix Timeline) ሰብረው ስለሚወጡ፣ አርከኖች (የመረቡ ጠባቂዎች) እንዳይገለጡ አግደዋቸዋል።
የ"መለኮታዊ ጦርነት" መዝሙራት፦
አርከኖችንና የጨለማ መናፍስትን በአንዴ የሚያቃጥሉ፣ የቴክኖሎጂ ሴራዎችን የሚያፈርሱና የሳተላይት ጨረሮችን የሚበጣጥሱ መዝሙራት አሉ።
የኢትዮጵያ "ሐመልማል" መዝገብ፦
እነዚህ 4,050 መዝሙራት በኢትዮጵያ ውስጥ "ሐመልማል" ተብሎ በሚጠራውና በስውራን ቅዱሳን እጅ ባለ መለኮታዊ መዝገብ ውስጥ በምስጢር ተጠብቀው ይገኛሉ።
ለምን 150 ብቻ ቀሩ?
ሥርዓቱ 150ውን ብቻ ያስቀረው፣ እነዚህ መዝሙራት ለሰው ልጅ "ሥነ-ምግባርና ምስጋና" ብቻ እንዲያገለግሉ ነው። "ትእዛዝ" እና "ሥልጣን" ያላቸው መዝሙራት ግን በ7 መቆለፊያ ተቆልፈው ተቀብረዋል።
ወዳጄ የታሰረው እውነት ይህ ነው፦ አንተ የምታውቀው መዝሙረ ዳዊት የባሕሩ ጠብታ ብቻ ነው። እውነተኛው የዳዊት መዝሙር 4,050 የብርሃን ሰይፎችን የያዘ መዝገብ ነው። የቀቡሩት ቅዱሳን ሳይሆኑ ማትሪክስ መሆኑ ይታወቅልኝ ። ቀጣይ በሰፊው እመለሳለሁ።
ቸር ያሰማን
0 Comments