፯ቱ (7ቱ) የቅድስ ያሬድ የሰማይ አዕማደ ዜማዎች" ምስጢር


✍  ዮሐንስ አብነት አጉማስ | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር

ሥርዓቱ (መረቡ) በሰባት መቆለፊያ የቆለፈውንና የሰው ልጅ አምላካዊ ኃይሉን ዳግም እንዳያገኝ የቀበረውን "፯ቱ (7ቱ) የያሬድ የሰማይ አዕማደ ዜማዎች" ምስጢር ላፍስልህ፦

ከመቃብር በታች የተቀበሩት ፯ቱ (7ቱ) የያሬድ መለኮታዊ ዜማዎች ቅዱስ ያሬድ ወደ ሰማይ ሲነጠቅ የሰማውና በምድር ላይ በምስጢር የዘራው ዜማ በጠቅላላው ሰባት (7) ነው። ሦስቱ ለሕዝብ ሲገለጡ፣ አራቱ ግን "ለነቁ ነፍሳት" ብቻ በምስጢር ተሸሽገዋል። እነዚህ ሰባቱ ዜማዎች ከሰባቱ ሰማያትና ከሰባቱ የሰውነት የኃይል ማዕከላት  ጋር የተቆራኙ የንዝረት ቁልፎች ናቸው። 

፩. ግእዝ (የመጀመሪያው ንዝረት - መሬት)፦

• ምስጢሩ፦ ይህ ዜማ ከሥጋዊ ፍጥረትና ከመሬት ንጥረ ነገር ጋር የተያያዘ ነው።

• ኃይሉ፦ ቁስን የማንቀሳቀስና በምድራዊ ነገር ላይ የመሰልጠን ኃይል አለው። 

፪. ዕዝል (የቤዛነት ንዝረት - ደም)፦

• ምስጢሩ፦ ከክርስቶስ ሕማማትና ከሰው ልጅ የዘር ግንድ (DNA) መጠገን ጋር የተያያዘ ነው።

• ኃይሉ፦ የሰው ልጅ እርግማንን የመስበርና ደምን የማንጻት ፍጹም ኃይል አለው። 

፫. አራራይ (የመንፈስ ንዝረት - አየር)፦ 

• ምስጢሩ፦ ከእርቅና ከሰላም ንዝረት ጋር የተያያዘ ነው።

• ኃይሉ፦ የታመመ ነፍስን የማረጋጋትና አየርን የመቆጣጠር ምስጢር ይዟል። 

፬ቱ (4ቱ) የተሰወሩ ዜማዎች (የመረቡ ትልቁ ፍርሃት) 

፬. ራማ (የብርሃን ንዝረት - ፬ኛው ሰማይ)፦

• ምስጢሩ፦ ይህ ዜማ "ራማ" ከተባለው ሰማይ የተቀዳ ሲሆን፣ የሰው ልጅ ከሥጋዊ ስበት (Gravity) ተላቆ በጠፈር ውስጥ የመመላለስ (Teleportation) ምስጢር ያለበት ዜማ ነው።

• ሥርዓቱ የደበቀው ለምን?፦ የሰው ልጅ ይህን ዜማ ቢዘምር፣ በመረቡ (በማትሪክስ) ውስጥ ተቆልፎ መኖር ስለሚያቅተውና እንደ መላእክት በብርሃን ፍጥነት መጓዝ ስለሚችል ነው። 

፭. መንክር (የተአምራት ንዝረት - ፭ኛው ሰማይ)፦

• ምስጢሩ፦ "መንክር" ማለት "ድንቅ/ተአምር" ማለት ነው። ይህ ዜማ የቁስን ባሕርይ የመለወጥ  ኃይል አለው። ውኃን ወደ ደም፣ ድንጋይን ወደ ዳቦ የመለወጥ ምስጢራዊ ንዝረት በዚህ ዜማ ውስጥ ይገኛል።

• ሥርዓቱ የደበቀው ለምን?፦ የሰው ልጅ በምግብና በቁስ ፈላጊነት ለሥርዓቱ ተገዢ እንዲሆን ስለሚፈለግ፣ ይህን "ራስን የመቻል" ማስተር ቁልፍ ቀብረውታል። 

፮. አርያም (የንጹሕ ብርሃን ንዝረት - ፮ኛው ሰማይ)፦

• ምስጢሩ፦ ይህ ዜማ የሰውን ልጅ ሥጋ ወደ "ብርሃን አካል" (Light Body) የመለወጥ ምስጢር ነው። ያሬድ ራሱ ሳይሞት የተሰወረው በዚህ ዜማ ንዝረት ውስጥ ገብቶ ሥጋው ስለቀለጠ ነው።

• ሥርዓቱ የደበቀው ለምን?፦ ሞት ሥርዓቱ (መረቡ) ሰውን የሚያስፈራራበት ትልቁ መሣሪያ ነው። ይህ ዜማ ግን ሞትን የሚሰርዝ የዘላለም ሕይወት "ባዮ-ኮድ" ነው። 

፯. ቅዱስ ቅዱሳን (የዙፋኑ ንዝረት - ፯ኛው ሰማይ)፦

• ምስጢሩ፦ ይህ የመጨረሻውና "የአልፋና ኦሜጋ" ዜማ ነው። ጊዜን የማቆም (Time Stasis) ኃይል አለው። ይህ ዜማ ሲሰማ አጽናፈ ዓለሙ ጸጥ ይላል፤ ጊዜም መቆጠሩን ያቆማል።

• ሥርዓቱ የደበቀው ለምን?፦ ማትሪክስ (መረቡ) የሚኖረው በጊዜ ዑደት ውስጥ ነው። ጊዜ ከቆመ መረቡ ይፈርሳል። ስለዚህ ይህ "የጊዜ ማቆሚያ" ዜማ ከሰው ልጅ ንቃት በ ፯ መቆለፊያ ተቆልፎ ተቀብሯል። 

የያሬድ "ምልክቶች" (Notation) ስውር ቴክኖሎጂ 

ያሬድ የተጠቀመባቸው ፲ሩ (10ሩ) ምልክቶች (ይዘት፣ ርክክ፣ ድፋት፣ ቅናት...) ተራ የዜማ መለኪያዎች አይደሉም። እነሱ "መለኮታዊ ቀመሮች" ናቸው፦

• ይዘት (Capture)፦ የአየር ላይ ኃይልን የመያዝ ኮድ።

• ርክክ (Connection)፦ ከሰማያዊው ሰርቨር (Throne) ጋር የመገናኛ ኮድ።

• ድፋት (Dissolve)፦ የጨለማ መጋረጃን የማፍረሻ ኮድ።

• ቁልፍ ምስጢር፦ እነዚህ ምልክቶች በብራና ላይ ሲቀመጡ የሚፈጥሩት ጂኦሜትሪ፣ የሰውን ልጅ የፒኒያል እጢ (መንፈሳዊ ዓይን) በአንዴ የመክፈት ኃይል አለው።

ወዳጄ  የታሰረውና የተቀበረው  እውነት ይህ ነው፦ ያሬድ ፫ ዜማ ብቻ ሳይሆን ፯ቱን የሰማይ መክፈቻዎች ሰጥቶሃል። 

ተዋህዶ እውነትና  ከሳይንስ በላይ ነች

ቸር ያሰማን!

Post a Comment

0 Comments