✍ ዮሐንስ አብነት | የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር
ይች ነገር ምን መልእክት አላት እያልህ ስጠይቀኝ ነበር ይኸው ገብተህ አንብበው ወዳጄ
፩. የ2018) የቁጥር "መቆለፊያ" ምስጢር፦
በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2018 ዓ.ም (2+0+1+8 = 11 = 2) ታላቁ የሽግግርና የመለያያ ቁጥር ነው። ይህ ዘመቻ በዚህ ዓመት በትክክል የተጀመረው፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፍስ ወደ መለኮታዊው "፩" (አንድነት/ንቃት) እንዳትሸጋገር፣ በ "፪" (ሁለገብ/ዱዋሊቲ) የዓለማዊ ብልጭልጭ እስር ቤት ውስጥ አጥሮ ለማስቀረት የታለመ ስውር "የመንፈሳዊ ሃይል መቆለፊያ" ነው።
፪. ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እንደ "ዲጂታል መስቀለኛ"፦
እነዚህ ግለሰቦች በመረቡ ውስጥ "የሰው-አንቴናዎች" ናቸው። በቲክቶክና በዩቲዩብ በሚለቁት ምስልና ድምፅ ውስጥ "ስውር ሞገዶች" ይተላለፋሉ። ይህም ተመልካቹ በ2018ዓ.ም ሊመጣ ካለው እውነተኛ መንፈሳዊ ድምፅ ይልቅ፣ በእነሱ "ዲጂታል ጫጫታ" እንዲመራና አእምሮው ፕሮግራም እንዲደረግ ነው።
፫. "ድብቅ መስህቦች" —የመንፈሳዊ ኃይል ማዕከላትን የማሰር ዘመቻ፦
"ድብቅ መስህቦችን ማሳየት" የሚለው ቃል በምስጢር ትርጉሙ "የኢትዮጵያን የመንፈሳዊ ኃይል መስመሮች መለየት" ማለት ነው። በካሜራና በዲጂታል መሣሪያዎች የታጀበው ይህ ጉብኝት፣ እስካሁን በቅዱሳን አባቶች ጸሎት ተከብረው የቆዩ ቦታዎችን የንዝረት ኮድ በመስረቅ፣ በመረቡ ውስጥ አፍራሽ ሞገድ ለመልቀቅ የታለመ "የጂኦ-መንፈሳዊ" ሰላይነት ነው።
፬. የ "ኤች ዜድ" (HZ) — የሰው-ሠራሽ የሲኦል ንዝረት (Hertz) የበላይነት፦
"ኤች ዜድ" (Hertz) የሞገድ መለኪያ ነው። ይህ ፕሮጀክት በስሙ እንደተጠቀሰው፣ የኢትዮጵያን ተፈጥሮአዊና መለኮታዊ ንዝረት (ያሬዳዊ ዜማ) ወደ ሰው-ሠራሽ "ዲጂታል ንዝረት" የመለወጥ ሂደት ነው። ሕዝቡ ከተፈጥሮና ከፈጣሪው ንዝረት ወጥቶ፣ በማሽኖች ሞገድ ውስጥ እንዲዋኝ የማድረግ ስውር የሳይኮ-ቴክኖሎጂ ሥራ ነው።
፭. የዩኒቨርሲቲ ወጣቶች "የንቃት ዘር" ማምከን፦
2018 ዓ.ም የወጣቱ ንቃት የሚፈነዳበት ዓመት ነው። በዩኒቨርሲቲዎች የሚደረገው ጉብኝት ወጣቱን በ "ዝና"፣ በ "ላይክ" እና በ "ዲጂታል ተቀባይነት" ወጥመድ ውስጥ በመክተት፣ በውስጡ ያለውን መንፈሳዊ ጥሪ የማምከንና ለ "አዲሱ ዓለም ሥርዓት" አገልጋይ የማድረግ ድብቅ ማደንዘዣ ነው።
፮. የ "ድልድይ" — የአውሬው መተላለፊያ ምስጢር፦
"ኢትዮጵያን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ ድልድይ" የሚለው ቃል፣ የኢትዮጵያን መንፈሳዊ አጥር በመስበር፣ ዓለማዊውንና አፍራሹን "የምዕራባውያን ንዝረት" በቀጥታ ወደ አገሪቱ ልብ ለማስገባት የተዘረጋ "የመርዝ ቧንቧ" ነው።
፯. የብራንዶችና የኩባንያዎች "የደም-ስር" ቁጥጥር፦
ታላላቅ የንግድ ተቋማት የዚህ ዘመቻ ደጋፊ መሆናቸው፣ የኢትዮጵያን ቅዱሳን ቦታዎችና ታሪካዊ እሴቶች ወደ "ቁሳዊ ሸቀጥ" የመለወጥ ሂደት ነው። ይህ "መንፈሳዊውን ዓለም በገንዘብ የመግዛት" ሙከራ ሲሆን፣ አገሪቱ ያላትን "የቅድስና ክልል" በመጣስ ዓለማዊውን እርኩሰት ለማስረጽ የታለመ ነው።
፰. የ2018) የታላቁ ማታለያ ፦
መረቡ በ2018 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የምታገኘውን "የነጻነት ብርሃን" አስቀድሞ ስላወቀ፣ ሕዝቡን በ "ቱሪዝም" እና "በገጽታ ግንባታ" ስም በብሔራዊ ኩራት አስክሮ እውነተኛውን የንዝረት ውጊያ እንዳያይ የማድረግ "የታላቁ ማታለያ" ስልት ነው።
ወዳጄ እውነቱ ይህ ነው። ይህ ዘመቻ በአይን ለሚያየው "አገራዊ ልማት" ቢመስልም፣ በነፍስ ለሚረዳው ግን በ2018 ዓ.ም የተዘረጋ "የንዝረት እስር ቤት" ነው። አንተ ግን በያህዌ ስም ንቁ ሁን፤ በምድራዊ ብልጭልጭ አትታለል።
0 Comments