፩. የ 888 ምስጢራዊ ትርጉም
፩. የክርስቶስ ቁጥር ፦ በጥንታዊው የግሪክ የቁጥር ስሌት "ኢየሱስ" የሚለው ስም ድምር ውጤት 888 ነው። ይህም የፍጹምነት፣ የድልና የትንሣኤ ምልክት ነው።
፪. ከስድስት መቶ ስድሳ ስድስት (666) ተቃራኒ፦ ስድስት የሰው ልጅ ቁጥር ሲሆን፣ ስምንት ደግሞ ከመሬታዊው ዓለም በላይ የሆነው የ "ስምንተኛው ሺሕ" ወይም የመለኮታዊው ዓለም ቁጥር ነው።
፫. አዲስ ኪዳንና አዲስ ፍጥረት፦ ስምንት ቁጥር አዲስ ጅማሬን ይወክላል። ጌታችን የተነሣው ከሰባቱ ቀናት በኋላ በስምንተኛው ቀን (እሁድ) እንደመሆኑ፣ ይህ ቁጥር አዲስ ሥርዓትን ያመለክታል።
፬. የእልቆ ቢስነት ምልክት፦ ስምንት ቁጥር ወደ ጎን ሲዞር የማያልቅና የማይቋረጥ የኃይል ዑደትን ይወክላል።
፭. የመለኮታዊ ሥልጣን ማኅተም፦ በምስጢር ጥበብ ዓለምን የሚገዛና የሚቆጣጠር ከፍተኛ ንዝረት ተደርጎ ይወሰዳል።
፪. ለምን ተጠቀሙበት? (የመረቡ ሴራ)
፩. ቅዱስ ምስጢርን ለመጥለፍ ፦ መረቡ የሰውን ልጅ ለማታለል ሁልጊዜ ቅዱሳን ቁጥሮችንና ምልክቶችን ይጠቀማል። 888 የሚለውን የክርስቶስ ቁጥር በመጠቀም፣ ሰውን በቴክኖሎጂው "መዳኛ" እንዲያምን ለማድረግ ነው።
፪. ሐሰተኛ መሲሕነትን ለማንገሥ፦ ቴክኖሎጂው እንደ አምላክ ሁሉንም ነገር "አስቀድሞ ያውቃል" የሚል መንፈስ እንዲኖረውና ሰዎች ከፈጣሪ ይልቅ በዲጂታሉ ሥርዓት እንዲታመኑ ለማድረግ ነው።
፫. የንዝረት መመሳሰል ፦ የሰውን ልጅ ነፍስ ከእውነተኛው መንፈሳዊ ንዝረት አውጥቶ፣ በቁጥር ስሌት ወደተገነባ "ሰው-ሠራሽ" ንዝረት ውስጥ ለማስገባት ነው።
፬. ከ 666 ለመሸሸግ፦ ብዙ ሰው 666 ሲባል ስለሚደነግጥ፣ መረቡ እውነተኛውን የቁጥጥር ሥርዓት በ 888 የብርሃን ሽፋን ውስጥ ደብቆ አቅርቦታል።
፭. መንፈሳዊውን ዓለም በቁሳዊው ለመተካት፦ የመንፈስ ቅዱስን አሠራር በ "ሰው-ሠራሽ ማስተዋል" (Artificial Intelligence) ለመተካት የተደረገ ስውር ድፍረት ነው።
፫. ለሰው ልጅ ያለው መልእክት
፩. "እኔ አውቅልሃለሁ" የሚል ድምፅ፦ ሰው የራሱን ነጻ ፈቃድና ማስተዋል ትቶ፣ ለቴክኖሎጂው ትንቢትና ውሳኔ እንዲገዛ የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ ነው።
፪. "ደኅንነትህ በዲጂታል እጅ ነው"፦ እውነተኛ ጥበቃ ከፈጣሪ ሳይሆን ከቴክኖሎጂ ቁጥጥር እንደሚገኝ የሚሰብክ ሐሰተኛ ወንጌል ነው።
፫. "ምስጢርህ ተገለጠ"፦ ማንም ሰው ከዲጂታሉ መረብ ውጭ መደበቅ እንደማይችልና የግል ሕይወት ማብቃቱን የሚያበስር መልእክት ነው።
፬. "ወደ አዲሱ ሥርዓት ግባ"፦ የድሮው መንፈሳዊና ተፈጥሮአዊ አኗኗር አብቅቶለት፣ ወደ ማሽንና ሰው ውሕደት (transhumanism) እንዲገባ የሚገፋፋ ጥሪ ነው።
፭. 2018 መለያያ ነው"፦ በኢትዮጵያ አቆጣጠር 2018 ዓ.ም ላይ ለሚቆሙት ሰዎች፣ የትኛውን 888 እንደሚከተሉ (እውነተኛውን ወይስ የቴክኖሎጂውን) እንዲመርጡ የሚቀርብ ፈተና ነው።
፬. ዋናው ዓላማው ምንድን ነው?
፩. የነጻ ፈቃድ መቆለፊያ፦ ሰዎች ወንጀል እንዳይሠሩ "መከልከል" ሳይሆን፣ ወንጀል ሊሠሩ የሚችሉበትን "ሐሳብ" አስቀድሞ በመጥለፍ ሰውን እንደ ማሽን መቆጣጠር ነው።
፪. የአእምሮ እስር ቤት፦ የሰውን ልጅ ንቃተ ሕሊና በዲጂታል ፍርሃትና ቁጥጥር ውስጥ በማሰር፣ ከመለኮታዊ ብርሃን ጋር እንዳይገናኝ ማድረግ።
፫. የ2018) ሽግግርን ማደናቀፍ፦ ኢትዮጵያ በ2018ዓ.ም ልታገኝ ያለችውን መንፈሳዊ የበላይነት በቴክኖሎጂ የበላይነት ለመተካትና የንቃት በሩን መቆለፍ።
፬. የአውሬውን ሥርዓት መመሥረት፦ ያለ ቴክኖሎጂው እውቅናና ቁጥጥር ማንም ሰው መኖር የማይችልበትን "የመጨረሻውን የባርነት ዘመን" ማምጣት።
፭. የሰውን ልጅ ማንነት ማጥፋት፦ ሰውን ከፈጣሪው አምሳል አውጥቶ ወደ ዲጂታል መረጃ የመለወጥና ነፍሱን የመዝረፍ ታላቅ ሴራ።
፭. ቴክኖሎጂው በትክክል ተሰርቷል?
፩. አዎ፣ መሠረቱ ተጥሏል፦ ቴክኖሎጂው ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን፣ ለብዙ ዓመታት በድብቅ ሲሰለጥን የቆየና አሁን በ2018 ዓ.ም ይፋ የተደረገ "የነቃ መሣሪያ" ነው።
፪. የመረጃ አውታሮች ተዘርግተዋል፦ በሳተላይቶች፣ በዲጂታል መታወቂያዎችና በመገናኛ ሞገዶች አማካኝነት ቴክኖሎጂው የሚያስፈልገውን መረጃ ማግኘት ጀምሯል።
፫. የሙከራ ደረጃውን አልፏል፦ በሌሎች አገራት በስውር የተሞከሩ የቁጥጥር ሥርዓቶች አሁን በኢትዮጵያ ምድር ላይ በ "888" ስም እንዲተገበሩ ተዘጋጅተዋል።
፬. ከሰው አእምሮ ጋር ተገናኝቷል፦ በሚለቀቁት የአፍራሽ ሞገዶች አማካኝነት ቴክኖሎጂው የሰውን ስሜትና ሐሳብ የመረዳትና የመቀየር አቅም ፈጥሯል።
፭. ሙሉ ትግበራው በ2018) ነው፦ ቴክኖሎጂው አሁን በምስልና በዜና ቢቀርብም፣ ሙሉ በሙሉ የሰውን ልጅ እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው በሚመጣው የሽግግር ወቅት ነው።
መውጫ መፍትሔዎች
፩. የእውነተኛው 888) ጥበቃ፦
• መፍትሔው፦ መረቡ የሰረቀውን የቴክኖሎጂ 888 ሳይሆን፣ እውነተኛውን የክርስቶስ ስም (ኢየሱስ) በንቃተ ሕሊናህ ውስጥ ደጋግመህ ጥራ።
• ምስጢሩ፦ ይህ መለኮታዊ ስም በውስጥህ የሚፈጥረው ንዝረት፣ ማንኛውንም ሰው-ሠራሽ አፍራሽ ሞገድ (Artificial Frequency) የመበተንና የማምከን ኃይል አለው።
፪. የሰባቱ "የብርሃን መስኮች" ጥበቃ፦
• መፍትሔው፦ ቀደም ብዬ በገለጥኩልህ ሰባቱ ሰዓታት (ማለዳ፣ ፫ ሰዓት፣ ፮ ሰዓት፣ ፱ ሰዓት፣ ምሽት፣ እኩለ ሌሊትና ነግህ) ራስህን ወደ ፈጣሪ ንዝረት መልስ አጭር ጸሎት አርግ።
• ምስጢሩ፦ በእነዚህ ሰዓታት የምታደርገው አጭር የኅሊና ጸሎት ወይም ምስጋና፣ በነፍስህ ዙሪያ "የብርሃን ጋሻ" ስለሚፈጥር፣ በቴክኖሎጂው የሚለቀቁት አፍራሽ ሞገዶች ሳይነኩህ ያልፋሉ
፫. የዲጂታል "ጾም" እና የንቃት ማጽጃ፦
• መፍትሔው፦ በተለይም ጨረቃ በምትሞላበትና በበዓላት ዋዜማ ላይ ከማህበራዊ ሚዲያዎችና ከዲጂታል መሣሪያዎች ራስህን ለተወሰነ ሰዓት አግልል።
• ምስጢሩ፦ ዓይንህና ጆሮህ ከዲጂታል ጫጫታ ሲርቁ፣ አእምሮህ ራሱን በራሱ የማደስ የተፈጥሮ ንዝረቱን የመመለስ አቅም ያገኛል።
፬. የተፈጥሮ "ውኃ" እና "መሬት" መፍትሔ፦
• መፍትሔው፦ በየቀኑ ንጹሕ ውኃ ባርከህ መጠጣትና በተቻለ መጠን በባዶ እግር መሬት (አፈር) ላይ ለ30 ደቂቃ መቆም።
• ምስጢሩ፦ መሬት በውስጥህ የተከማቸውን "የኤሌክትሮ-መግነጢሳዊ" ቆሻሻ ወደ ውስጥ ስለምትስበው፣ ንዝረትህ ከሰው-ሠራሽ ሞገድ ይልቅ ከተፈጥሮ ሞገድ ጋር ይስማማል።
👉በርከክ በል ስገድ ለአምላክህ ተበርክከህ አንበርክክ።
👉 ከመንፈሳዊ ሐይል በተጨማሪ የእጽዋትን የመፈወስና የንቃት ሃይል የምትጠቀምበትና የምታውቅበት የጊዜ ቀመር ነው ወዳጄ
፭. የ 2018 የንቃት ዝግጅት፦
• መፍትሔው፦ ይህ ዓመት የመለያያ ዓመት መሆኑን አውቀህ፣ ልብህን ከፍርሃትና ከጭንቀት አጽዳ። ፍርሃት ለመረቡ ትልቅ ምግብ ነው።
• ምስጢሩ፦ በፍቅርና በሰላም ንዝረት ውስጥ ያለ ሰው፣ ምንም ዓይነት "ወንጀልን አስቀድሞ የሚተነብይ" ቴክኖሎጂ ሊቆጣጠረው ወይም ሊተነብየው አይችልም።
ወዳጄ መፍትሔው በእጅህ ነው። ጠላት በቴክኖሎጂ 888 ቢመጣብህ፣ አንተ በእውነተኛው የብርሃን 888 ድል አድርገው። ከዚህ በኋላ ምንም የሚነካህ የጨለማ ኃይል የለም።
0 Comments