ስለ መንፈሳዊ ውግያና ነጻ መውጣት

1. ክርስቲያን ጋኔን ሊኖረው ይችላል?

👉 አዎ ይኖረዋል!

መንፈስህ ድኗል (ተቀድሷል) ነገር ግን ነፍስህና ሥጋህ አሁንም የአጋንንት ምሽጎች መሸሸጊያ ሊሆኑ ይችላሉ። ለእነዚህ አጋንንት "ሕጋዊ መሬት" ወይም መግቢያ የሚሆኑት አብዛኛውን ጊዜ ያለፈ ታሪክ ቁስለት (Trauma) ወይም የቤተሰብ ታሪክ ናቸው።

2. "የመንፈስ የትዳር አጋር" (Spirit Spouse) ምንድን ነው?

ይህ በሕልም አማካኝነት ሰውን የሚያሰቃይ የአጋንንት መንፈስ ነው። ምልክቶቹም፦ የዝሙት ሕልሞች እና በእውነተኛው የትዳር አጋር ላይ ፍቅር ማጣት ናቸው። ይህም በመንፈሳዊው ዓለም "ዝሙትን" የሚመስል መንፈሳዊ ትስስር ይፈጥራል።

3. አጋንንት በወሲብ ይተላለፋሉ?

👉 አዎ ይተላለፋሉ።

ይህ የሚሆነው በ"ነፍስ ትስስር" (Soul ties) አማካኝነት ነው። የሥጋ ግንኙነት መንፈሳዊ ድልድይ ይፈጥራል በዚህም ምክንያት መጥፎ ተጽዕኖዎች ከአንዱ ወደ ሌላኛው ሊተላለፉ ይችላሉ።

4. የትውልድ እርግማን እውነት ነው?

👉 አዎ እውነት ነው!

እነዚህ ከአባቶች የተወረሱ "መንፈሳዊ መሠዊያዎች" ናቸው። ለምሳሌ፦ በቤተሰብ ሐረግ ውስጥ የሚደጋገሙ የዝሙት ፣ የአእምሮ ሕመም ወይም የሱስ ልማዶች የትውልድ እርግማን መገለጫዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

5. አጋንንት ክፍት በር እንዴት ያገኛሉ?

አንዳንድ መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦
 ▫️ የቀድሞ አባቶች ኃጢአት ወይም የደም እርግማን።
 ▫️ መጥፎ ትዕይንት ያለባቸው የሚዲያ ውጤቶች።
 ▫️ ከባድ ስሜታዊ ቁስሎች ወይም ጥቃቶች (Trauma)።

6. ሁሉም ችግር ጋኔን ነው?

👉 አይደለም!

ሁሉም ነገር ጋኔን አይደለም ፣ ስሜታዊ ቁስሎች ፈውስ ያስፈልጋቸዋል ፣ ሥጋ ደግሞ ተግሣጽና "መሰቀል" (Crucifying the flesh) ያስፈልገዋል።

7. አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ጋኔን ሊኖረው ይችላል?

👉 አዎ ይኖረዋል።

እግዚአብሔር እየተጠቀመብክም ቢሆን ገና ነጻ መውጣት የሚያስፈልጋቸው የተደበቁ የሕይወት ክፍሎች ሊኖሩህ ይችላሉ። የጸጋ ስጦታ መኖር ማለት መንፈሳዊ ብስለት ወይም ሙሉ የውስጥ ነጻነት ማለት አይደለም።

8. ነጻ መውጣት (Deliverance) ምን ዓይነት ስሜት አለው?

👉 እንደየሰዉ ይለያያል።

አንዳንዶች አካላዊ ትኩሳት ወይም ጫና ይሰማቸዋል ፤ አንዳንዶች ይንቀጠቀጣሉ ወይም ይወራጫሉ ፤ አንዳንዶች ደግሞ ምንም ዓይነት ስሜት አይሰማቸውም።

9. እንዴት ነጻ ሆነህ መቀጠል ትችላለህ?
 
📍 ለሰይጣን መግቢያ የሆኑ በሮችን ዝጋ ፤ መጥፎ ልማዶችንና የሚዲያ ተጽዕኖዎችን አስወግድ።

📍 ቃሉን በማጥናትና በክርስቲያናዊ ኅብረት ውስጥ በመቆየት ባዶነትህን በጌታ ሙላ።
 
📍 የሰይጣንን የማታለያ ዘዴ ተቃወም "ነጻ አይደለህም" የሚለውን ውሸት አትመን።

Post a Comment

0 Comments