የሰብአዊ መብት አያዎ፦ የሴቶች ጥቃት ተኮንኖ ውርጃ ተወድሶ!



✍ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር

የሴቶች ጥቃት ግድያም (Femicide) ይቁም ብለው ሕጻናቱን ግን መግደል (Infanticide) መብትና ነፃነት የሚያደርገው “አዋቂ” ምን ያክል ሰውነቱ የጠፋበት ልባልባም ቢኾን ነው? ውርጃ የሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም እጅግ የከፋ ግፍ፣ ኃጢያት፣ ወንጀልም ነው!

(ChatGPTም ኾነ Gemini የጽሑፌን ሃሳብ በተለመደው መልኩ ገልጬላቸው ምስል ስጡኝ ብላቸው ሃሳብህ ከ guidline ጋር ይቃረናል አሉ። ለምን? ይህ ከዚህ በፊት ከጉግል ያወረድኩት ነው።
ስለ የሰው መብት በተለይም ስለ ሴቶች ጥቃት “እናሳስባችሁ” የሚሉን ሰዎች ሕጻኖቻችንን በመብትና ነፃነት ስም እንድናጠፋ የሚያስተምሩን ናቸው።

ኢትዮጵያውያንን ስለ ሰብአዊ መብት ለማስተማር ሆዳደር ልሂቃኑንና ሊቃውንቱን ይዘው “ግብር በማይከፍሉ ሱቆቻቸው” (ግብረሰናይ ተቋማት) በኩል የተሰማሩት ምዕራባውያን በተለይም እንግሊዝ በመብት እና ነፃነት ስም ሊወለዱ ደቂቃዎች እስከቀራቸው ሕጻናቱ ድረስ ማስወረድን በሕይወት ክህሎት (Life Skill, SRHR) የሚያስተምሩን ናቸው።

እነዚህ በመብትና ነፃነት ስም ዳጎስ ያለ ገንዘብ ይዘው፣ ከቤተመንግሥት እስከ ቤተክህነት የሆዳደሮች መረብ ዘርግተው ትውልዳችንን ለማጨናገፍ የመጡ ተቋማት ከዚህ በፊት እንደምነግራችሁ ነባር የኾነው መልካሙን መልካም፣ ልኩን ልክ፣ ተገቢውን ተገቢ፣ ውቡን ውብ የሚለውን እሴት በሌላ ባዲስ ለመተካት የሚራወጡ ናቸው።

ስለዚህም በተቀደሰ መኝታውም ንጹሕ በኾነ ትዳር ልጆችን ማምጣቱን “መልካም ነው” ከማለት ይልቅ፤ አንዲት ሴት ሥራና ትምህርቷ በእርግዝና ምክንያት እንዳይጨናገፍ ልጇ ሊወለድ ደቂቃዎች ሲቀሩትም ማስወረድ መልካም ነው ብለው ያስተምራሉ።

እንደ አባወራ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ዝም ማለት አይገባንም። ልጆቻችንን፣ እህቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንን በዚህ ልብ አጥፊ ክፉ ባህል ቁጥጥር ስር እንዳይኾኑ መፍጠን አለብን።

ማርክሳዊ ግራምሺያውያን ይህንን ውጤቱ ጥፋት የኾነ የባህል ወረራን ቤተክርስትያን ድረስ ባሏቸው ልባልባ ሊቃውንት ይዘውት ገብተዋል።

በዚያም ሴቶቻችን ሲያረግዙ የሚከፋቸው፣ እርግዝና በሽታቸው፣ ወሊድ መቆጣጠሪያ መድኃኒታቸው፣ ውርጃም ግልግላቸው ኾኖ በቅድስቲቷ ሀገር የሕጻናት ደም ለአጋንንት “በባለሙያ የተማሩ ባለልምድ” አውራጆች ይፈሳል ይሰዋሉ።

“የሰብአዊ መብት” ስሙ ለክፋት ሥራቸው ካባ (Camouflage) ነው። የሰብአዊ መብት የማይቆረቁረው በተለይም የሴቶቹ፣ ሲቀጥልም የአካል ጉዳተኞች (ማርክሳውያን ሸፍጠኞች የሚያስቀድሙት ቅደም ተከተል ነው) አሁን ደግሞ የአየር ንብረት ጉዳይ የማያሳስበው ይኖር ይኾን?

አዎን! ሁሉም ታቅዶበት ትውልድን ለማጥፋት ማኅበረሰብን ለማምከን የመጡ ናቸው! ይህንን በመልካም ስም የመጣን የአጋንንት ሥራ ማስቆም የሚችለው፦

👉 ከአምላኩና ከአባቱ ጋር የተጣበቀ፣

👉 ጽድቁን ይፈጽምበት ክፉን ያርቅበት ዘንድ በጸጋው ላይ የሠለጠነ፣

👉 በጨውነት ጣዕሙ የተገለጠ፣

👉 መስዋዕት እስኪኾን ነፍሱን ለወዳጆቹ የሰጠ፣ አባወራ ብቻ ነው!

🚨 በዘመናዊነት እና መንፈሳዊነት ሰበብ እንከፍ ምስኪን፣ ጃንደርባ፣ አስመሳይ፣ አድርባይ፣ አላዛኝ ነፍራቃ... የኾነው አይችልም። ይኹን እንጂ ያስመስላል፣ ከጠላት ጋር ተደራድሮ በጎቹን በማስበላት የአንድ ሰሞን እፎይታን ያመጣ ይኾናል።

ነገር ግን በራሱ ስሜት፣ ፍላጎት፣ ብልትና አእምሮም ላይ አልሠለጠነምና ይህ ለእርሱ የሚርቅበት፣ ለሃሳቡም የሚረቅበት ይኾናል!

ወንድሞቼ! ይህ ክፉ ሥራ ስር እየሰደደ ነው፤ ልጆቻችን በሚሰማሩበት በዐለሙ ብቻ አይደለም፤ እንደውም ጽድቁን ይማሩ ዘንድ ከሚሄዱበት ቤተክርስትያንም ጭምር እንጂ!

ጽንስን እስኪወለድ ጠብቆ ማስወረድ “የሴቷ መብትና ነፃነት ነው፤ ይህንን የሚከልከል ደግሞ የሴቷን ገላ እንደ ንብረቱ ሊቆጣጠር የሚፈልግ አባወራውና ሥርዓቱ ነው” ይሉናል!

እንዲህ ነው የUN እና የግብር አበሮቹ መርሕ፦ ነባሩን፣ ትውልድ ያነጸዉን እሴት ንዶ፤ በሌላ ቃዲስ የትውልዱን ልብ አጥፍቶ ለመቆጣጠር በሚያበቃው መተካት (cultural hegemony) የሚለውን የግራሞሺን ንድፍ የተከተለው።

ስለዚህም ይህንን፦

🌟 ስር የሰደደ፣

🌟 ሴቷን በራሷ ገላ ላይ ነፃነት እንዳይኖራት፣

🌟 ልጆቿን በመርዝ በጣጥሳ በመቀስ ቆራርጣ መግደልን የሚከለክላት፣

🌟 መከልከሉም እንደ ጾታዊ ጥቃት ተቆጥሮ፤

🌟 ጨካኝና በዳይ የኾነ “አባወራዊ ሥርዓት” ማስወገድ እንደሚገባ ያስተምሯቸዋል።

ሴቶቻችን ብሶት ተበጥብጦ፣ ብሶት ተጠምቆ፣ ብሶት ሲጋቱ ኖረው ትዳር፣ ቤተሰብ፣ ወንድ የማያምኑ፣ የሚርቁ፣ የሚጠሉ፤ ነገር ግን የማንም ሳይኾኑ ከማንም፣ ለማንም የትም እግራቸውን የሚያነሱ፣ የሚፈጠረውንም ጽንስ በመርዝ በጣጥሰው በመቀስ ቆራርጠው የሚያጠፉ፤ ይህም መብትና ነፃነቻቸው እንደኾነ የሚሰማቸው ይኾናሉ።

እነዚያ ግብር የማይከፍ ሱቅ ያላቸው ሆዳደር ሊቃውንት በግብረሰናይ ተቋማቸው ስለ ሰብአዊ መብት ሲደሰኩሩ፦

👉 በጦርነት የሚረግፉ፣

👉 በረሃብ አለንጋ የሚገረፉ፣

👉 በአስተዳደር በደል የሚገፉ፣

👉 በሽፍታ የሚገፈፉ ሴቶቻችንን ጉዳይ አይመለከታቸውም።

ምክንያቱም እነዚህ በጾታዊ ጥቃት ስም የአባወራውን ልብ ለመስለብ፣ ወኔ ቢስ አልጫም ለማድረግ፣ ከልጆቹና ከቤተሰቡ ለማራቅ አይጠቅሙምና።

ከዚያ ይልቅ ግን ከቤት ትምህርት ቤት በተማሪ ሰርቪስ ወይም በታክሲና በቤት መኪና የምትመላለሰውን፣ ስለ ጾታዊ ጥቃት ምንም የማታውቀውን፦

➡️ የትም ከማንም መንጠላጠሉ መብቷ፣

➡️ “በሽታ” በኾነው እርግዝና እንዳትያዝ መከላከያ መቃም ነፃነቷ፣

➡️ በዚህ “ክፉ በሽታ” ብትያዝም እንደ እጢ አፍርጠውና ቆራርጠው ሊያወጡላት ቃል የገቡላትን ሰምታ በአባቷና በባሏ ላይ የምታምጽ ሴትን ያፈራሉ እንጂ።

ይህ የዘመናችን የሰብአዊ መብት ነው። አንድም ይህ የዘመናችን ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች የሚቆሙለት አጀንዳ ነው። አንድም ይህ በሰብአዊ መብት ስም ከቤተመንግሥት እስከ ቤተክህነት ድረስ የ”ይለፍ” ቃል የተሰጠው ልጆቻችን እየተጋቱት፣ ትውልድ እየጠፋበት፣ ማኅበረሰብም እየመከነበት ያለ ማርክሳዊ፣ ግራምሺያዊ፣ የግራዘመሞች የጥፋት ትርክት ነው!

🌟 እኛ የሚስቶቻችን፣ የልጆቻችን፣ የቤተሰባችን፣ የማኅበረሰባችን ጠባቂ ባለ አደራዎች ይህ በእኛ፣ የእኛ በኾኑት ሁሉ ዘንድ እንዲፈጸም አንፈልግምና እንቃወመዋለን!

🌟 በዚያም የተሰጠንን ወንድነት መክሊቱን ጽድቁን መፈጸም ወደሚችል አባወራዊ ልዕልና በማንሳት የምንከላከለው፣ የምናስወግደውም ይኾናል!💪






Post a Comment

0 Comments