ወንዱን ሁሉ ሰልበው ሲያበቁ “ሴቷ ከወንዱ ትሻላለች” ይላሉ፤ እነ ሆድ አምላኩ!

ሔኖክ ኃይለገብርኤል | አባወራ | ኢትዮጵያ አውታር

አድርባይ ሊቃውንቱ “መንፈሳዊነት” ብለው የሚግቱን መርዝ፣ ወንዱን ስልብ ጃንደርባ በማድረግ፤ ውጤቱ እንደ እንግሊዟ ቤተክርስትያን ጥፋት ለኾነው ርዕዮተ-ዓለም አሳልፎ ለመስጠት የታለመ ስውር ደባ ነው።

“ሊቃውንቱ” ያመጡት፣ የሚመሰክሩት፣ ያቀረቡትም የወንዶቻችን ስልብነትና የሴቶቹ “ልበሙሉነት”
በቤተ መቅደሳችን ቅጥር ውስጥ እየታየ ያለው ።ትልቁ ክህደት፣ በሥርዓተ አምልኮ ሽፋን የሚቀርብ የትውልድ ስልበት ነው።

ሆድ አምላካቸው” የኾኑትና ለውጭ ርዕዮተ-ዓለም ቅጥረኛ የሆኑት አድርባይ ሊቃውንት፣ በመጀመሪያ ወንዱን ከማንነቱ፣ ከጀግንነቱና ከአባወራነት ክብሩ ነጥለው “ልባልባ” አድርገውታል።

ወንዱ ለክብሩ እንዳይቆም፣ ለጽድቅ እንዳይጨክንና የመቅደሱን ቅጥር እንዳይጠብቅ በአጉል መንፈሳዊነት ስም ወኔውን ሰልበውታል።

ወንዱን እንዲህ አላምጠውና አድቅቀው ማንነቱን ካጠፉት በኋላ፣ አዙረው ደግሞ “ወንዱ የማይረባ ነው፣ ፈዛዛ ደካማ ነው፤ ሴቷ ከወንዱ ትሻላለች፣ በአመራርም ትበልጣለች” የሚል ሸንጋይ አጥፊ መርዛቸውን ይረጫሉ።

ወንድሞቼ! ይህ አካሄድ በአጋጣሚ የመጣ ሳይኾን፣ ሃይማኖታችንን ከውስጥ ደርምሶ፣ ማርክሳዊው ርዕዮተ-ዓለም ሰተት ብሎ እንዲገባ ምቹ የማድረግ ስውር ስልት ነው።

አባወራነት የቤተሰብና የሃይማኖት የመከላከያ ግንብ ነው። ይህ ግንብ ሲፈርስ፣ መቅደሱ ለፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሙከራዎች፣ የበግ ለምድ ለሚለብሱ ተኩላዎች ክፍት ይሆናል።

ሊቃውንቱ “የጾታ እኩልነት” እያሉ የሚግቱን ቃል፣ ወንዱን ከመሪነትና ከጠባቂነት ሥልጣኑ አውርዶ ለማንም ታዛዥ ጃንደርባ የማድረግ ስውር ዓላማ ያለው ነው።

ወንዱ ደመቀዝቃዛ፣ ስልብ ኾኖ መሪነቱን ሲተው፦ ቤቱ፣ ቤተ-መቅደሱ፣ ቤተ-መንግሥቱ አባታዊ ግርማውን ያጣል፤ ያኔ ባዕድ ርዕዮተ-ዓለሞች እንደ ልባቸው የሚፈነጩበት “የወንበዴዎች ዋሻ” ይኾናል።

እነዚህ አስመሳይ አድርባዮች በትውልዱ ላይ የሚፈጽሙት ደባ በአንድ በኩል

👉 ወንድ ልጅ ለአያት ቅድመ አያቶቹ ጀግንነትና ጽድቅ እንዳይናፍቅ፣ ይልቁንም በታሪኩ እንዲሸማቀቅ፤ አንድም ወንድነት ተፈጥሮውን ኮንነው በጡንቻውና በወኔው እንዲያፍር በማድረግ አልጫ፣ ስልብ፣ ጃንደርባ ኾኖ እንዲኖር ይሰብኩታል።

በሌላ በኩል ደግሞ

👉 ወንዱ ስልብ ኾኖ ሲመክን፣ እንከፍ ኾኖ ምስኪን ሲኾን ተቋማቱን (ቤተሰብንና ቤተክርስትያንንም) ሴት-መር ለማድረግ ቀስ በቀስ መለኮታዊውን ሥርዓት ሴታቆርቋዥ ለኾነው(Feminism) ለዓለማዊ ድርጅቶች አጀንዳ አሳልፈው ይሰጣሉ።

“የሴቶች አመራር በቤተክርስትያን” በሚለው ዘመን ተሻጋሪ የጥፋትጨመድረካቸው የቅድስት ሥላሴ ሊቀ-ሊቃውንት በአመራር ከወንዱ ሴቷ እንደምትሻል ሲደሰኩሩ ሴቶችን ለማክበር ሳይኾን፣ ወንዱን አሳንሶ መቅደሱን ያለ ጠባቂ ለማስቀረት የሚጠቀሙበት የሽንገላ መሣሪያ ነው።

እውነተኛ አባወራ ባለበት ስፍራ፣ ባዕድ አጀንዳዎች አይሰርጉም፤ እውነተኛ ልባም ትውልድ ባለበት መቅደስ፣ ሆዳደር ሊቃውንት ቦታ የላቸውም።

ለዚህ ነው መጀመሪያ ወንዱን “ልባልባ” ለማድረግ ጀግንነትና ክብር ከሚወደስበት፣ ጀግኖች ከሚዘከሩበት እሴቱ መለየት ያስፈለጋቸው። ይህ በቤተክርስቲያን ላይ የተደገሰ ታላቅ አደጋ ነው፤ ትውልዱን ከመንፈሳዊ መሪነት አውጥቶ ለባርነት የማዘጋጀት ስትራቴጂም እንጂ!

በመኾኑም፣ ይህንን የአድርባይ ሊቃውንት ስውር ደባ ነቅቶ ማጋለጥ ይገባል። ልባም ትውልድ የሚነሳው እነዚህ ሆዳደሮች ወንድነቱን ሊሰልቡት ሲሞክሩ፣ እርሱ ግን በአያቶቹ ጽኑ እሴት ላይ ቆሞ “መቅደሴንና ክብሬን አሳልፌ አልሰጥም!” ብሎ ሲጨክን ነው።

ወንዱ ዳግም አባወራ ኾኖ ካልተነሳ፣ መቅደሱ በሸቃጭ ለዋጭ ነጋዴዎች መጠለፉ አይቀሬ ነው። ትውልዱ ከስልብነት ነቅቶ ወደ ቀደመው ክብሩ ይመለስ ዘንድ የአባወራው መለከት ሊነፋ ይገባል!

Post a Comment

0 Comments