ትውልዴ ልብ አልባ ኾኖ እየጠፋ መኾኑ እንዳይታወቀው የደነዘዘበት ልክ የግራምሺያኑን ረቂቅና ስውር የባህል ወረራ ውጤማነት ያሳያል። ንቁ! አትነዱ!
ወገኔን ለማደንዘዝ ማርክሳውያንና ግራምሺያውያን የተጠቀሙት ስልት ትውልዱ ባልጠበቀው፣ ማኅበረሰቡም ባልጠረጠረው መንገድ የተጎነጎነ የባህል ወረራ ነው።
ይህ የባህል፣ የእሴት፣ የማንነት ወረራው የመጣው በ”ሰብአዊ መብት”፣ በ”እኩልነት”፣ እና በ”ዘመናዊነት” ስም ስለኾነ፣ ማኅበረሰቡ እንኳን ሊጠነቀቀው መርዙን ራሱ እንደ መድኃኒት እየተሻማ እንዲወስደው ኾኗል።
አንድ ማኅበረሰብ “ጸጥ” የሚለው ጠባቂዎቹና መሪዎቹ (አባወራዎቹ) ትውልዱን ወደ ጽድቅ ከመምራት ሲደክሙ ወይም ሲሰንፉ ግድ የለሽም ሲኾኑ ነው። በዚያም ወንዱ “አልጫ” እና “ጃንደርባ” እንዲኾን በተሰበከው ስብከት ምክንያት፣ “ምን አገባኝ?” ባይነትና የግል ምቾቱን ብቻ መፈለግ ይጀምራል።
ቢናገርና ቃላት ቢወጣው እንኳ “አርፈህ ኑሮህን አትኖርም? ልጆችህን አታሳድግም?” የሚል የአድርባዩ “ተቆርቋሪነት” ኾኗል። ቤተሰብ ሲፈርስ፣ ሀገርም የመፈራረስ አደጋ ሲጋረጥባት፣ “እኔን ካልነካኝ” የሚል የባርነት ሥነ-ልቦና እንጂ አስተዋይ ብልህነት አይደለም።
እጅግ የሚገርመው ሴትነትንና እናትነትን እንደ “እስር”፣ አባወራነትንና ወንድነትን ደግሞ እንደ “ጭቆና” እንዲቆጠር ይህንንም ልጆቻችን እንዲማሩት ሲደረግ፣ ይህም አደጋ እንዳለው እየተነገረን እንኳ መፍዘዝ መደንዘዛችን ነው።
አንዲት ሴት ልጅ የገዛ ማኅፀኗን እንድትጠላ፣ ጽንሷን በመርዝ በጣጥሳ በመቀስ ቆራርጣ ማስወረድን እንደ መብትና ነፃነት ሲሰበክላት፣ ማኅበረሰቡ ዝም ብሎ ማየቱ ትልቁ የድንዛዜው መለኪያ ነው። ተፈጥሮን፣ ራስን ፈጣሪንም መጥላት፦ ዐዲሱ ዘመናዊነት!
እናት የገዛ ማኅፀኗን እንደ እስር ቤት እንድትቆጥር፣ አባት ደግሞ የቤቱ፣ የሚስቱ፣ የልጆቹ ጠባቂነቱን ትቶ እንከፍ ምስኪን፣ ጃንደርባም እስኪኾን ድረስ “ዘመናዊነት መንፈሳዊነትም ነው “ በሚል ስብከት መደንዘዙ ሳያንስ፤
እርሱን አንስቶ ለሚሞግተው ሁሉ “አንተ ከሊቀ-ሊቃውንት እንቶኔ ትበልጣለህ?” እያለ እርሱ ልብአልባ ኾኖ ባፍጢም ተደፍቶ ዝም ባለበት ዝም ሊያሰኝ ይወራጫል!
ታላቁ ምሁር ቶማስ ሶዌል(እባካችሁ መፍሐፉን ካገኛችሁ አንብቡ አልያም ቃለመጠይቁን ስሙ፤ የተለመዱ ፖድካስቶች ላይ አይቀርብም) በግልጽ እንዳሳየው፣ የጥቁር አሜሪካውያን ትልቁ ጠላት ዘረኝነት ሳይኾን “አባት-አልባ” የቤተሰብ መዋቅር ነው።
ምን አለ?
🚨 የጥቁር አሜሪካውያን ትልቁ ጠላት ዘረኝነት ሳይኾን “አባት-አልባ” የቤተሰብ መዋቅር ነው።
ድገመው👇
🚨🚨 የጥቁር አሜሪካውያን ትልቁ ጠላት ዘረኝነት ሳይኾን “አባት-አልባ” የቤተሰብ መዋቅር ነው።
ለሦስተኛ ጊዜ👇
🚨🚨🚨 የጥቁር አሜሪካውያን ትልቁ ጠላት ዘረኝነት ሳይኾን “አባት-አልባ” የቤተሰብ መዋቅር ነው።
ይህም ኾን ተብሎ ተፈጸመ!
(ዝምታችን ያሰጋል የጤናም አይመስልምና ስለዚህ በሚቀጥለው ጨምሬ እጽፍበታለሁ)
ቶማስ ሶዌል በጥቁሩ ማኅበረሰብ ላይ የታዘበውና እኛም ያነሳነው ነጥብ—አባትን ከቤት አስወጥቶ በመንግሥት ድጎማና በሕፃናት ማቆያ መተካት—ትውልድን ከእውነት፣ እምነትና እሴቱ ነጥሎ “ልብ-አልባ” አድርጎታል።
ወገን ልጆቹን ለባዕድ እሴት አሳልፎ እየሰጠ፣ “መንግሥት ያበላልኛል፣ ትምህርት ቤት ያስተምርልኛል” በሚል ሰባራ ተስፋ መደንዘዙ፣ የነገውን የልጆቹን ባርነትና ጥፋታቸውን ዛሬ በአስር ጣቱ እየፈረመ መኾኑን አለማወቁ ነው።
እኛ ጋር እየኾነ ያለው ይሄው ነው! መንግሥትና ተቋማት የቤተሰብን ድርሻ እንዲተኩ ፈቅደን፣ አባወራውን “እንከፍ አልጫ፣ ስልብ ጃንደርባ፣ አጨብጫ፣ ታይታና ይኹንታ ፈላጊ” አድርገን ነገ የምናመርተው ትውልድ የባርነት እንጂ የነፃነት አይኾንም!
የሚገርመው ወንድ ልጅ ሚስቱን፣ ልጆቹንና ቤተክርስቲያኑን በነፍሱ ተወራርዶ እንዳይታደግ ወኔውን የሚሰልቡ ባፍጢም የተደፉ፣ ሊቅና ሊቀ ሊቃውንት የተባሉ ሆዳደር “የሞት ነጋዴዎች” በየመድረኩ፣ ያውም በቅዱሱ ስፍራ መሰየማቸው ነው።
ለትውልዱም በተለይም ለወንዱ ወንድነት አባወራነትን ከጥንካሬና ድፍረቱ፣ ከሥልጣኔና ጉልበቱ ለይተው ለስላሳ፣ ቀለስላሳ ለጆሮ ደስ የሚል ነገር ግን ለባርነት የተመቸ አድርገው የሚሸቅሉበት፣ እነርሱም ወደፊት የሚገፉት ካለምክንያት አይደለም።
🚨 ኾን ተብሎ ነው!
ወንድን ልጅ “አልጫና ምስኪን” የሚያደርግ ስብከት በየመድረኩ ሲዘራ፣ አባወራነትን በአስመሳይ አድርባዮች መስፈሪያ እየተለካ ሲናኝ ማኅበረሰቡ በተለይም ወንዱ እንዲደነዝዝ የተላከ ጦር መኾኑን ማን አስተዋለ?
ትውልዱ ጠባቂ የሌለው መንጋ ለተኩላ የተመቸ መኾኑን ዘንግቶታል፤ ትዳር የሚፈርስበት መርዙን እንደ መድኃኒቱ የሚግቱት የተማመነባቸው “አዋቂዎች” ልጆቹን በእኩልነት መብትና ነፃነት ሰበብ፣ በዘመናዊነትና በመንፈሳዊነትም ስም ሲሸቅጧቸው፣ ሲለውጧቸው፤ ጠላት ደግሞ ለባርነትና ሞት ይናጠቃቸዋል።
ይህ ድንዛዜ ተራ መዘናጋት ሳይኾን፣ ሰውነት የሚበየንበት ልብን ሰልቦ ሥጋን ብቻ እንደ እንሰሳ የሚያኖር ረቂቅ እና ስውር ሴራ ነው።
ይህንን የትውልድ ጥፋቱን ከሌሎች ዓይተንና ሰምተን ስናበቃ፣ በዝምታ ስናልፈው፦ ልባአልባ ሰዎች ጥቂት የምንለይ ከእንሰሶች ኾነናል ማለት ነው!
ድንዛዜው ይብቃ!
ከተኛንበት እንንቃ!
ዝምታችን ይሰበር!
🚨 ትውልድ እያጣን ነው!
🚨 ቤተሰብ እየፈረሰ ነው!
🚨 ልጆቻችን እየተበተኑ ነው!
🚨 ጋብቻ ትዳራችን መጠቋቆሚያ እየኾነ ነው!
🚨 ትዳርን ታናናሾቻችን እየፈሩት እየጠሉትም ነው!
🚨 ምን ቢማር ዶክተርና ኢንጂነር፣ ሊቅና ሊቀ ሊቃውንት ቢባል አልጫና አስመሳይ አድርባይ ሆዳደርም ትውልድ እያፈራን ነው!
🚨 የጠላቶቻችን መሳቂያና መሳለቂያም እየኾንን ነው!
🚨 ማኅበረሰባችንም እየመከነ ነው!
🚨 ሆዳደር ምሁራን ደግሞ በቁማችን እየነገዱብን ነው!
0 Comments