በኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ወቅት 3፣ 6፣ 9፣ 11 እና 12 ቁጥሮች የነበራቸው መለኮታዊ አስተዋጽኦና ከመጋረጃ ጀርባ ያለው ምስጢራዊ ትርጉም ከጥልቁ መዝገብ


✍ ዮሐንስ አብነት የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር

👉ማሳሰቢያ  / እነዚህን ቁጥሮች ስታነብ በጊዜ አቆጣጠር ባላቸው በስዓት ልኬት አድርገህ ተረዳ 

👉ቁጥር 3 - ምሰጢር 

በመስቀል ላይ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ለሦስት ሰዓታት ዓለምን የሸፈነው ጨለማ፣ የሥላሴን ምስጢርና መለኮት በልጁ መከራ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ የሚያሳይ ነው። ይህ ሦስት ቁጥር ፀሐይ ፈጣሪዋ ሲሰቃይ ለማየት ባለመፈለጓ ንዝረቷን የገታችበትና የአጽናፈ ዓለምን መጋረጃ ለሦስት ሰዓታት የጋረደችበት መለኮታዊ የጊዜ ኮድ ነው። 

በጎልጎታ ላይ የቆሙት 3 መስቀሎች (የክርስቶስና የሁለቱ ወንበዴዎች) የሰው ልጅን አጠቃላይ ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ ናቸው። በመሃል ያለው የክርስቶስ መስቀል የሕይወት ዛፍ ሲሆን፣ በግራና በቀኝ ያሉት ደግሞ የፍርድና የምሕረት ምልክቶች ናቸው። ይህ ሦስት ቁጥር ዓለም በሦስት ዓይነት ንቃት (በክህደት፣ በንስሐና በጽድቅ) መካከል መከፈሏን ያሳያል። 

በመስቀል ራስ ላይ የተጻፈው ስም በሦስት ቋንቋዎች (በዕብራይስጥ፣ በግሪክና በላቲን) መሆኑ፣ ጌታችን ለሦስቱ ክፍላተ ዓለምና ለሰው ልጅ ሁሉ ንጉሥ መሆኑን ያበሰረበት ነው። ይህ 3 ቁጥር መለኮታዊው የምሥራች በሦስቱ የምድር አቅጣጫዎች ዘልቆ በመግባት የድንቁርናን መቃብር የፈነቀለበት መለኮታዊ ግንኙነት ነው። 

ጌታችን በመስቀል ላይ የዋለው በሦስተኛው ሺህ (በግማሽ) መሆኑና በሦስተኛው ቀን ከመቃብር መነሣቱ፣ ቁጥር ሦስት የድልና የትንሣኤ ማኅተም መሆኑን ያረጋግጣል። በመስቀል ላይ በደረሰው መከራ ሦስቱ የሰው ልጅ ጠላቶች (ዲያብሎስ፣ ኃጢአትና ሞት) የተሸነፉበት ምስጢራዊ ቀመር ነው። 

3 ቁጥር በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ደምና ውሃ እንዲሁም መንፈስን (ምስክሮቹን) የሚያመለክት ነው። እነዚህ ሦስቱ ምስክሮች በምድር ላይ የታተመውን የሞት ኮድ ሰርዘው በመለኮታዊ የሕይወት ንዝረት የተኩበትና የሰው ልጅን ነፍስ ከማትሪክስ እስራት ነፃ ያወጡበት የጥልቁ መዝገብ እውነት ነው። 

👉ቁጥር 6 -ምስጢር 

ጌታችን በመስቀል ላይ የተቸነከረው በስድስት ሰዓት (ቀትር) ላይ ነው። ይህ ስድስት ቁጥር ሰው የተፈጠረበትን ስድስተኛ ቀንና ሰዓት የሚያመለክት ሲሆን፣ በመጀመሪያው ስድስት ሰዓት የተሳሳተውን አዳምን በሁለተኛው ስድስት ሰዓት በመስቀል ላይ ሆኖ መልሶ የፈጠረበትና የቀደሰበት መለኮታዊ የጥገና ጊዜ ነው። 

6 ቁጥር የሥጋዊ ፍላጎትና የምድራዊ ድካም ምልክት ቢሆንም፣ ክርስቶስ በስድስት ሰዓት በመስቀል ላይ መቸንከሩ ግን የሥጋን ፈቃድ በመለኮታዊ ፈቃድ የገዛበት ነው። ይህ ቁጥር በሰው ልጅ ዲ ኤን ኤ ውስጥ የነበረውን የውድቀት ንዝረት ሰብሮ በመስቀሉ ኃይል ወደ ከፍተኛ የብርሃን ንቃት የቀየረበት ምስጢር ነው። 

በ6 ሰዓት ፀሐይ ጨልማለች፤ ይህም ማለት 6ቁጥር የጨለማው ግዛት ከፍተኛው ጫፍ ላይ የደረሰበትና በመለኮት መከራ የተሰበረበት መሆኑን ያሳያል። ጌታችን በስድስት ሰዓት በመስቀል ላይ በመቆሙ፣ በስድስቱ ክፍላተ ዘመን (5500 ዘመናት) የነበረውን የኃጢአት ዕዳ በአንድነት ደምስሶታል። 

በመጨረሻም 6ቁጥር የመስቀሉ አራት ማዕዘናትና የሁለቱ (የመለኮትና የትስብእት) ውሕደት ድምር ነው። ይህ ቁጥር በመስቀል ላይ የዋለው ቃል ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ መሆኑንና በ6 ሰዓት የደረሰው መከራ ለአጽናፈ ዓለም ሁሉ ፈውስ መሆኑን የሚያረጋግጥ የመጨረሻው መዝገብ ነው። 

👉 ቁጥር 9 - ምስጢር 

ጌታችን በመስቀል ላይ ነፍሱን አሳልፎ የሰጠው በ9 ሰዓት ላይ ነው። ይህ 9 ቁጥር የሥራን ፍጻሜና የድልን ጫፍ የሚያመለክት ሲሆን፣ ጌታችን "ተፈጸመ" ብሎ ሲጮኽ በጠፈር ውስጥ የነበረው የጨለማ ንዝረት ተቀዶ የገነት ደጆች የተከፈቱበት መለኮታዊ ቅጽበት ነው። 

የ9ኙ ነገደ መላእክት ምልክት ነው። ጌታችን በ9 ሰዓት ነፍሱን ሲሰጥ፣ ዘጠኙ ነገደ መላእክት በመስቀሉ ዙሪያ ለድል አድራጊው ንጉሥ ክብር የሰጡበትና የሰው ልጅ ነፍስን ከሲኦል መቃብር ፈንቅለው ወደ ብርሃን ያወጡበት ምስጢራዊ ሰዓት ነው። 

በ9 ሰዓት የተሰማው መለኮታዊ ጩኸት የምድርን መሠረት ያናወጠው፣ ቁጥር 9 ከምድራዊው ንዝረት ወጥቶ ወደ ሰማያዊው "እልቆ ቢስ" ንቃት መሸጋገሪያ በመሆኑ ነው። ይህ ቁጥር በመስቀል ላይ የነበረውን መከራ ወደ ትንሣኤ ብርሃን የለወጠ መለኮታዊ ድልድይ ነው። 

የሰው ልጅ 9 ወር በማሕፀን ተጸንሶ እንደሚወለድ ሁሉ፣ የሰው ልጅ በክርስቶስ ሞት አማካኝነት ዳግም የተወለደበትን ምጥ ያሳያል። በ9 ሰዓት የፈሰሰው ደምና ውሃ የሰው ልጅ የዘላለም ሕይወት የሚያገኝበት የመንፈሳዊ ማሕፀን ምስጢር ሆኖ ተገልጧል። 

በመጨረሻም 9 ቁጥር የመለኮታዊ ፍቅር ጣራ ነው። ጌታችን እስከ ዘጠኝ ሰዓት በመስቀል ላይ መቆየቱ፣ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር እስከ ፍጻሜው ማሳየቱን ያረጋግጣል። ይህ ቁጥር ዛሬም በነፍሳችን ውስጥ ያለውን የጨለማ መጋረጃ ቀዶ ወደ መለኮታዊው ብርሃን እንድንገባ የሚጠራን የዘጠኝ ሰዓት የድል ዜና ነው። 

ቁጥር 11 - ምሰጢር

በመስቀል ላይ ካለው ከቀኝ ወንበዴ ንስሐ ጋር በቀጥታ ይገናኛል። በ11ኛው ሰዓት እንደመጣ ሠራተኛ፣ ይህ ወንበዴ "በመንግሥትህ አስበኝ" ባለ ጊዜ መጋረጃው ተቀዶለታል። ቁጥር 11 የሰው ልጅ ተስፋ በቆረጠበት ሰዓት መለኮታዊ ምሕረት የሚገለጥበት ምስጢራዊ ኮድ ነው። 

በመስቀል ስር የነበሩት 11ዱ ቅዱሳን ሐዋርያት (ይሁዳ በመወገዱ) የቤተክርስቲያን መሠረት ሆነው የተቆጠሩበት ሰዓት ነው። ይህ 11 ቁጥር ከጥፋት የተረፈውን ቅዱስ ዘርና በግርፋቱ ደም የታጠበውን አዲስ ትውልድ የሚያመለክት የመለኮታዊ ምርጫ ምልክት ነው። 

የሕግ መታደስና የጸጋ መብዛት ምልክት ነው። ከአሥሩ ትእዛዛት (10) በኋላ የሚመጣው 11ኛው ቁጥር፣ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰጠውን "እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ" የሚለውን አዲስ ትእዛዝ (11ኛውን ሕግ) በደሙ ያተመበት ምስጢር ነው።

በመጨረሻም 11 ቁጥር ከጨለማ አለም ወጥቶ ወደ መለኮታዊው አንድነት (1) የመመለሻ መንገድ ነው። 11 ሲደመር 2 (1+1) እንደሚሰጠን፣ ይህ ቁጥር በመስቀል ላይ የተገለጠውን የአምላክና የሰው ፍጹም ተዋሕዶና ሰላም የሚያበስር የጥልቁ መዝገብ እውነት ነው። 

ቁጥር 12 - የፍጹምነት እና የአጽናፈ ዓለም ሥልጣን ምስጢር 

ጌታችን በመስቀል ላይ በዋለበት ወቅት የነበሩት 12ቱ ሰዓታት (6 የብርሃንና 6 የጨለማ) አጠቃላዩን የሥነ ፍጥረት ጊዜ የሚወክሉ ናቸው። ይህ 12 ቁጥር ክርስቶስ የጊዜና የዘመን ጌታ መሆኑን፣ በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ደግሞ በሁሉም ሰዓታትና ዘመናት ለሚኖሩ የሰው ልጆች እንደሚሠራ የሚያረጋግጥ ነው። 

12 ቁጥር የ 12ቱን ነገደ እስራኤል (አጠቃላዩን የሰው ልጅ) በመስቀል ስር የመሰብሰብ ምስጢር ነው። ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ እጆቹን ሲዘረጋ፣ በ 12ቱ አቅጣጫዎች የተበተነውን የሰው ልጅ ወደ አንድ መለኮታዊ ማዕከል የሳበበትና የመቃብር ድንጋዩን የፈነቀለበት መለኮታዊ ሥልጣን ነው። 

በመስቀል ላይ የተገለጠው የ 12 ቁጥር ምስጢር፣ ጌታችን ሊጠራቸው ይችል ከነበሩት 12ቱ አእላፍ መላእክት (ማቴዎስ 26፥53) ይልቅ መከራን መምረጡን ያሳያል። ይህ ምርጫው የሰውን ልጅ ነፃነት ለመግዛትና የጨለማውን ኃይል በታላቅ ትዕግሥት ለመርገጥ የተጠቀመበት የመለኮታዊ ጥበብ ቁልፍ ነው። 

12 ቁጥር የሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም 12 ደጆች በመስቀሉ ኃይል መከፈታቸውን ያበስራል። ጌታችን በመስቀል ላይ ነፍሱን ሲሰጥ፣ እነዚህ 12 ደጆች ለነቁና ለተቀደሱ ነፍሳት ክፍት ሆነዋል። ይህ ቁጥር የሰው ልጅ ወደ ዘላለም ርስቱ የሚመለስበት የብርሃን መስመር ነው።

ቁጥሮቹ ከኒቆላ ቴስላና ከአጽናፈ ዓለም ንዝረት ጋር ያላቸው ትስስር 

ኒቆላ ቴስላ 3፣ 6 እና 9 ቁጥሮችን "የአጽናፈ ዓለም ቁልፎች" ብሎ የጠራቸው፣ እነዚህ ቁጥሮች በመንፈሳዊው ዓለምና በቁሳዊው ዓለም መካከል ያሉ የኃይል መስመሮች መሆናቸውን በንቃት ስለተረዳ ነው። እነዚህ ቁጥሮች በጠፈር ውስጥ የሚዘዋወረውን መለኮታዊ ንዝረት  እና ኃይል  የሚቆጣጠሩ መሠረቶች ናቸው።

ቴስላ 3-6-9 የሚለውን ቀመር የተጠቀመው፣ ይህ ቀመር ከሥጋዊው ዓለም ስበት ወጥቶ ወደ "ከፍተኛ ንቃት" ለመድረስ የሚያስችል ቁልፍ መሆኑን ስላወቀ ነው። ይህ ምስጢር መሠረቱ ከመጽሐፈ ሄኖክና ከአባቶች ጥንታዊ የከዋክብት ዕውቀት (አቡሻኽር) የተቀዳ ቢሆንም፣ ሳይንስ ግን ምስጢሩን በቁስ ደረጃ ብቻ ለመረዳት ሞክሯል። 

ቁጥር 11 እና 12 በቴስላ ስሌት ውስጥ የ "ጊዜ" እና የ "ቦታ" መለኪያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ ቁጥሮች የአጽናፈ ዓለምን የግንኙነት መረብ የሚዘረጉ ናቸው። ቴስላ የኤሌክትሪክ ኃይልን ያለ ገመድ ለማስተላለፍ ሲሞክር፣ የተጠቀመው በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ያለውን "የጠፈር ንዝረት" ነው። 

3-6-9 በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ያለውን "መለኮታዊ ጂኦሜትሪ" የሚወስኑ ናቸው። ቴስላ እንደተረዳው፣ እነዚህ ቁጥሮች በየትኛውም የቁስ አካል ውስጥ ያለውን አቶም የሚቆጣጠሩና ከሰማያዊው "የቃለ መለኮት" ንዝረት ጋር የሚያገናኙ "የኃይል ድልድዮች" ናቸው። 

ቴስላ እነዚህን ቁጥሮች ያገኘው በኢትዮጵያ ጥንታዊ ገዳማት ውስጥ ካሉት የብራና መጻሕፍት በሚወጣው "ረቂቅ ንዝረት" አማካኝነት መሆኑን ነው። ቸር ያሰማን ዮሐንስ

Post a Comment

0 Comments