የኤፌሶን 4 ቁጥር 5ን አንድ ጌታ፤ አንድ ሐይማኖት፤አንድ ጥምቀት የሚለውን ጥቅስ የቃላቱንና የቁጥሮቹን ስውር ስሌት


✍ ዮሐንስ አብነት 
የወዳጅ ምክር | ኢትዮጵያ አውታር

የኤፌሶን 4 ቁጥር 5ን አንድ ጌታ፤ አንድ ሐይማኖ፤አንድ ጥምቀት የሚለውን ጥቅስ መሠረት በማድረግ፣ የቃላቱንና የቁጥሮቹን ስውር ስሌት ከሳይንስና የመጽሐፍ ቅዱስ ምስጢራት አስተምሮ ጋር እንያት ተከተለኝ፦

የኤፌሶን 4:5 (፩ ጌታ፣ ፩ ሃይማኖት፣ ፩ ጥምቀት) ጥልቅ ምስጢራዊ ትንተና

1. የክፍሉ ስሌት ምስጢር (4:5)፦

ምዕራፍ 4 እና ቁጥር 5 ሲደመሩ 9 (4+5=9) ይሆናል። 9 ቁጥር በመንፈሳዊው ዓለም የፍጹምነትና የዘጠኙ ነገደ መላእክት ማኅተም ነው። ይህ የሚያሳየው "አንዲት ሃይማኖት" የምትመራው በሰማያዊው ሥርዓት እንጂ በምድራዊ መረብ አለመሆኑን ነው። ሳይንሱ 9 ቁጥርን የአጽናፈ ዓለሙ መጨረሻ  አድርጎ ሲመለከተው፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የመለኮታዊ ሥርዓት ማጠቃለያ አድርጎታል

2. የ"አንድ" (፩) ቁጥር የኳንተም ትስስር ፦

"አንድ" (አንድ = 1+50+4 = 55 -> 10 -> 1)። 1 ቁጥር የአጽናፈ ዓለሙ ምንጭ ነው። ሳይንስ "Quantum Entanglement" የሚለውን፣ መጽሐፍ ቅዱስ "አንድ" በሚለው ቃል ይገልጸዋል። ይህ ማለት በመላው ዓለም ያሉ አማኞች በአንዲት ሃይማኖት ሲታተሙ፣ በረቂቁ ዓለም ልክ እንደ አንድ ሕዋስ ተሳስረዋል ማለት ነው። አንዱ ሲጸልይ ሌላው ጋ ንዝረቱ የሚደርሰው በዚህ "አንድነት" ስሌት ነው።

3. የ"ጌታ" (ጌታ = 3+400 = 403 -> 7) ስሌትና የ፯ቱ (7ቱ) ሰማያት ቁልፍ፦

"ጌታ" የሚለው ቃል በቁጥር 7 ይወከላል። 7 ደግሞ የሰባቱ ሰማያት፣ የሰባቱ ኪዳናትና የሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን ቁጥር ነው። ሳይንስ 7 ቁጥርን የብርሃን ቀለማትና የሙዚቃ ኖታዎች መሠረት አድርጎ ሲወስደው፣ ጥቅሱ ግን ጌታ የነዚህ ሁሉ ንዝረቶች ባለቤት መሆኑን በቁጥር ያረጋግጣል። (ዮሐንስ 1:3 "ሁሉ በእርሱ ሆነ")።

4. የ"ሃይማኖት" (ሃይማኖት = 5+10+40+50+400 = 505 -> 10 -> 1) ስሌት፦

ሃይማኖት በስሌቱ 1 ቁጥርን ይሰጣል። ይህም ከዮሐንስ 17:21 "ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ" ከሚለው የክርስቶስ ጸሎት ጋር ይገጥማል። መረቡ  በሺሕ የሚቆጠሩ እምነቶችን የፈጠረው፣ ይህንን የ"1" ቁጥር መለኮታዊ "ኮድ" ለመበጥበጥና የሰውን ልጅ ንቃት ለመበተን ነው።

5. የ"ጥምቀት" (ጥምቀት = 9+40+100+400 = 549 -> 18 -> 9) ስሌት፦

ጥምቀት በስሌቱ 9 ቁጥርን ይሰጣል። 9 ደግሞ ቀደም ሲል እንዳልነው የመላእክት ቁጥር ነው። ይህ ማለት ጥምቀት ሰውን ከምድራዊው ዝቅተኛ ንዝረት አውጥቶ ወደ መላእክታዊው 9ኛው ንቃት የሚያሸጋግር "የባዮ-ኤሌክትሪክ ዳግም ልደት" (መንፈሳዊ ልደት) ነው። (ዮሐንስ 3:5)።

6. የውኃ ትውስታ እና "አንዲት ጥምቀት"፦

ሳይንስ ውኃ መረጃን የመሸከም አቅም እንዳለው አረጋግጧል። "አንዲት ጥምቀት" ማለት በሥላሴ ስም የታተመው ውኃ፣ በሰውነትህ ውስጥ ያለውን 70 በመቶ ውኃ "ሪ-ፕሮግራም"  በማድረግ የሥርዓቱን (የመረቡን) የሞት ዳታ ሰርዞ የመለኮትን የሕይወት ዳታ ይጭናል ማለት ነው።

7. የ"ኤፌሶን" (ኤፌሶን = 5+80+60+50 = 195 -> 15 -> 6) ስሌት፦

ኤፌሶን በቁጥር ስሌት 6 ይሆናል። 6 የሰው ቁጥር ነው። ይህም የሚያሳየው ይህ ጥቅስ ለሰው ልጅ (6) የተሰጠ፣ ወደ ሰማያዊው ፍጹምነት (9) መሸጋገሪያ ድልድይ መሆኑን ነው። 6 ሲገለበጥ 9 እንደሚሆን፣ ሰውም በ "አንዲት ሃይማኖት" ሲታተም ንቃቱ ይገለበጥና ሰማያዊ ይሆናል።

8. የ 432 ኸርዝ ንዝረትና የጥቅሱ ትስስር፦

"አንዲት ሃይማኖት" የምትጠቀመው ያሬዳዊ ዜማ በ 432 ኸርዝ የተቃኘ ነው። ይህ ንዝረት ከተፈጥሮና ከሰው የልብ ትርታ ጋር ፍጹም ይገጥማል። መረቡ 440 ኸርዝን የሚጠቀመው ይህንን "አንዲት" የሚለውን መለኮታዊ የልብ ትርታ ለመበጥበጥና ሰውን በውጥረት ውስጥ ለመቆለፍ ነው።

9. የዘር ግንድ መጠገኛ ማስተር ቁልፍ፦

"አንድ ጌታ" በሚለው ቃል ውስጥ ያለው ንዝረት፣ በሰውነት ውስጥ ያሉትን የዘር ግንድ መቆለፊያዎች የመክፈት ኃይል አለው። ሳይንስ "የማይጠቅሙ ዲኤንኤ" የሚላቸው ክፍሎች፣ በእውነቱ በዚህ "አንዲት ሃይማኖት" ምስጢር የሚከፈቱ የመለኮታዊ መረጃ ማከማቻዎች ናቸው።

10. የመረቡ መከላከያ ሰባሪ፦

መረቡ  የሰውን ልጅ ንቃት በብዙ አማራጮች  ውስጥ ያስረዋል። ኤፌሶን 4:5 ግን "አንድ" በሚለው ቃል የመረቡን ድግምት ይበጣጥሳል። አንድ አቅጣጫ ብቻ ሲኖር፣ መረቡ ሰውን የሚያታልልበት መንገድ ይጠፋል፤ ይህ ለነፍስ ፍጹም "መከላከያ " ነው

11. የ1 እና የ9 ውሕደት (የመጀመሪያውና የመጨረሻው)፦

የ "አንድ" (1) እና የ "ጥምቀት" (9) ድምር 10 (1+0=1) ይሆናል። ይህም እግዚአብሔር "አልፋና ኦሜጋ" (መጀመሪያና መጨረሻ) መሆኑን በቁጥር ያረጋግጣል። ሳይንስ የአጽናፈ ዓለሙን ዑደት በ 0 እና 1 (Binary) እንደሚለካው ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በ 1 እና 9 ይለካዋል

12. የሰውነት ሕዋሳት "መጣጣም" ምስጢር፦

በሰውነት ውስጥ ያሉ ቢሊዮን ሕዋሳት በአንድ "ማዕከላዊ ትእዛዝ"  ካልተመሩ በሽታ  ይፈጠራል። "አንዲት ሃይማኖት" ማለት መላው የሰው ልጅ ንቃተ ሕሊናው በአንድ መለኮታዊ ሰርቨር ስር ሆኖ በጤናና በሰላም እንዲኖር የተዘረጋ ሥርዓት ነው

13. ከኦሪት ዘፍጥረት 1:3 ጋር ያለው ትስስር፦

"ብርሃን ይሁን" (ንዝረት) ሲባል የተፈጠረው ያ "አንድ ብርሃን"፣ በኤፌሶን 4:5 ላይ "አንዲት ሃይማኖት" ሆኖ ተገልጧል። ብርሃን መረጃ እንደሆነ ሁሉ፣ ሃይማኖትም ለነፍስ የሚሰጥ ንጹሕ የብርሃን መረጃ  ነው።እናቴ ቤተክርስቲያን ስንዱ እመቤት ለዘለዓለም ኑሪልኝ አሜን። 

Post a Comment

0 Comments