እንዲ መላው የአለም ሕዝቦች በሙሉ (የፕሮቴስታንት የካቶሊክ የሙስሊም እምነት ተከታዮች) በሙሉ ተጠምቀው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ለመሆን የተዋሕዶ ልጆች ለመሆን እንዲ በጉጉት በሚጠብቁበት በዚህ ወቅት የኛዎቹ መሃይማን ግን ማርያምን (የአምላክን እናት) የመስቀል ስር ስጦታችንን አታማልድም አናከብራትም አንወዳትም እያሉ ጻድቃን ሠማዕታትን እንዲሁም ቅዱሣን መላዕክትን አንቀበልም አናከብርም እያሉ ሲዘሉ ሲንደባለሉ ሰይጣን ሲጨፍርባቸው ይውላሉ!!!
ያው ማታ ማታ ሞቅ ሲላቹህ እውቀት ያገኛቹህ እየመሰላቹህ ኦርቶዶክስን የምታሟት በደብተራዎቿ ምክንያት ነው!!! የእናንተ ትልቅ እውቀት መተት ነው።
ጠንቋይ መተታም ናቸው እያላቹህ ታወራላቹህ!!!
እውነት ነው ቄሶች እና ደብተራዎች ልዩ የሆነ አስማታዊ ጥበብ አላቸው!!!
እውነት ነው ቤተ ክርስቲያን ለቄሶችና ለደብተራዎች ልዩ የሆነ የአስማት ጥበብ ታስተምራቸዋለች።
ነገር ግን የምታስተምራቸው ሠዎችን ከደዌ ከበሽታ እንዲፈውሱ ከአጋንንት እስራት ከመተት እስራት እንዲጠብቁ ሠዎችን እንዲያክሙበት ነው እንጂ እንዲጎዱበት አይደለም!!!
አንድ ዶክተር ወደ እርሱ የመጣውን በሽተኛውን ማዳንም ሆነ መግደል ይችላል!!! ምክንያቱም ሠውን እንዴት ማዳን እንዳለብህ ስትማር ሠው እንዴት ለምን እንደሚሞት መማርህ አይቀርምና መድሀኒት ቅመማ ስትማር መርዝም መቀመም አይጠፋህም ስለዚህ ሠውን ማከም ማዳን የሚችለው ዶክተር ሠውን መግደልም እንደሚችል መቼስ አይጠፋህም ስለዚህ ዶክተሮች ገና ለገና ሠውን መግደል ይችላሉ ብለህ ዶክተሮች አያስፈልጉም ትላለህን???
ደብተራዎች አንድን ሠው ከእርኩሳን መናፍስት እስራት እንዴት ማዳን እንደሚችሉ ቤተ ክርስቲያን በደንብ አስተምራቸዋለች!!! በእርኩሳን መናፍስት ላይም ስልጣን ሰጥታቸዋለች። የሠውን ልጆች ከደዌ ከበሽታ ከእርኩሳን መናፍስት እስራት ለማዳን የሚያስፈልጉትን ጥበቦች አስማቶች በሙሉ አስተምራቸዋለች!!!
ነገር ግን አንዳንድ ደብተራዎች ይኼንን የሠጠቻቸውን ጥበብ ለመጥፎ ነገር ሊጠቀሙበት ይችላሉ!!!
እንዳልኳቹህ ቫይረስን እንዴት መግደል እንዳለበት የተማረ ሠው ቫይረስን እንዴት መፍጠርና ለመጥፎ ሁኔታ መጠቀም እንዳለበት ጭምር ያውቃል ስለዚህ እርሱ ዶክተሩ እውቀቱን ለመጥፎ ነገር ስለተጠቀመበት ሌሎች ዶክተሮችን ማስተማር አያስፈልግም ትላለህን???
አንዳንድ ግለሰቦች በግላቸው አማካኝነት በሚሰሩት ሀጥያት ምክንያት ምንም የማታውቀውን መላዋን ቤተ ክርስቲያንን መዝለፍ በሎጂክ አመክንዮ ሕግ Hasty Generalization የሚባለውን ፋላሲ መፈጸም ማለት ነው!!!
እናት ቤተ ክርስቲያን ግን ይኼንን የልጆቿን ጥፋት ስለምታውቅ ገና ድሮ ቀድማ ፀበል የሚባል መድሓኒትን በመፍጠር (ሁሉንም አይነት በሽታዎች ደዌዎች ሁሉንም አይነት የአጋንንት እስራትን መፍታት ማላቀቅ የሚችል የትኛውም አይነት ደብተራ የሰራውን መተት የሚያፈርስ ቋጠሮውን የሚፈታ) ፀበል የሚባል መድሓኒት ሠርታ አዘጋጅታ ኑ ልጆቼ እባካቹህ ፀበል ተጠመቁ ለደዌ ስጋ ለደዌ ነፍስ መድሓኒት ነው እያለች ዘውትር ትለምናለች!!! የሚሰማት የለም እንጂ
እንደ እኔ በመተት የተሰቃየ ምድር ላይ እንደ እኔ ብዙ መተት የተመተተበት ሠው አታገኝም!!!
ጠላቶቼ አምስቱ የፍልስጤም መንግስታት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ በዛ መተታቸው አስረው እያሰቃዩኝ ነው!!!
እንደ እኔ በመተት የተሰቃየ ምድር ላይ እንደ እኔ ብዙ መተት የተመተተበት ሠው አታገኝም!!!
ነገር ግን እኔ አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያን ላይ አኩርፌ አላውቅም!!! ምክንያቱም አይምሮዬ ያገናዝባል የጎዱኝ ግለሰቦች እንጂ እናት ቤተ ክርስቲያን አይደለቺም!!!
እናት ቤተ ክርስቲያንማ ይኼንን የልጆቿን ጥፋት ስለምታውቅ ገና ድሮ ቀድማ ፀበል የሚባል መድሓኒትን በመፍጠር (ሁሉንም አይነት በሽታዎች ደዌዎች ሁሉንም አይነት የአጋንንት እስራትን መፍታት ማላቀቅ የሚችል የትኛውም አይነት ደብተራ *የሰራውን *መተት *የሚያፈርስ *ቋጠሮውን *የሚፈታ) ፀበል የሚባል መድሓኒት ሠርታ አዘጋጅታ ኑ ልጆቼ እባካቹህ ፀበል ተጠመቁ ለደዌ ስጋ ለደዌ ነፍስ መድሓኒት ነው እያለች ዘውትር ትለምናለች!!! የሚሰማት የለም እንጂ
ስለዚህ እናት ቤተ ክርስቲያን ንጹሕ ናት ፍጹም ናት!!!
እናም እጃችሁን ከቤተ ክርስቲያን ላይ አንሡ ክሳችሁንም አቋርጡ!!!
ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው እንዲሉ አበው "ጆሮ ያለው ይስማ - ልቦና ያለውም ያስተውል - እምቢ የሚልም እምቢ ይበል" ተብሎ እንደተጻፈ በፍጥነት ንስሐ በመግባት ወደ እናት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተመለሡ!!! ሳይረፍድባቹህ ማለት ነው!!!
አለበለዚያ ግን ፈጣሪያችን አምላካችን ንጉሣችን አባታችን ልዑል እግዚአብሔር ክርስቶስ መድኃኔዓለም በእናንተ ላይ የቅጣት መቅሰፍቱን ይልክባቹሀል!!!
"ጆሮ ያለው ይስማ - ልቦና ያለውም ያስተውል - እምቢ የሚልም እምቢ ይበል" ተብሎ እንደተጻፈ
0 Comments