አውስትራሊያዊው ትውልድ ራስ ጠልነትን ተግቶ፣ እሴት ትውፊቱን አጥቶ ራሱን የሚገድል፣ ዘሩን የሚያመክን፣ አእምሮውንም ያጣ፣ ጭንቀታም እንዲኾን በትምህርት ቤት ሳይቀር ተግቷል።
ኦዚ= Aussie= Australia
አንቶኒዮ ግራምሺ እንዳለው የአንድን ማኅበረሰብ አርበኛዊ ወኔና የማንነት መሠረት(እሴት) ለመናድ የግድ በጦር መሣሪያ አብዮት ማፈንዳት አያስፈልግም፤
ይልቁንም በፊት የነበረውን፣ ተቋማትን የገነባውን፣ ማኅበራትን ያጸናውን፣ ቤተሰብን ያቆመውን ነባር ትርክት፣ ትውፊት፣ እሴት በትምህርት ቤቶችና በቤተ ክርስቲያን ሰርጎ በሚገባ “የራስ ጠልነት” ትርክት በመተካት የትውልዱን ወኔ መስለብ ይቻላል።
ትናንት በበረሃና በውቅያኖስ መካከል ተጋድሎ ሀገር ያቀናው፣ የሥልጣኔ አውታር የዘረጋው አርበኛዊ መንፈስ ዛሬ በገዛ ሀገሩ ባይተዋር እንዲኾን ተፈርዶበታል።
ይህ ስልታዊ የወንድነትና የአርበኝነት ስሜትን መስለብ ትውልዱን ከመጣበት እሴቱና ለኑሮ ከሚታጠቀው ድፍረቱ ለይቶ “ልባልባ” አድርጎታል።
በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ ሳይቀር “ብሔራዊ ስሜት” እንደ ወንጀል፣ “አርበኝነት” ደግሞ እንደ “መርዛማ፣ አጥፊና አጥቂ ወንድነት” ተቆጥሮ እንዲሰጥ መደረጉ፣ ወጣቱ ኦዚ ስለ አባቶቹ ጀግንነት ከመኩራት ይልቅ በታሪኩና በማንነቱ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ አድርጎታል።
(በቅርቡ አንድ ታዋቂ አውስትራሊያዊ ወጣት በትምህርት ቤት የተማረውንና ራሱን ከመጥላቱ የተነሳ እርሱም ኾነ ሌሎች ኦዚዎች ለጭንቀትና ራስን ለማጥፋት ጭምር የገፋፋቸውን አስታውሶ፤ ይህንን ትውልድን የማኮላሸት ሸፍጥ አጋልጧል)
ይህ የታሪክ ጥፋተኝነት ሸክም ትውልዱን አእምሮውን እንዲያጣና በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንዲወድቅ በማድረግ፣ ራሱን እስከ ማጥፋት ለደረሰ የሥነ-ልቦና ቀውስ አጋልጦታል።
የአባቶቹን ጀግንነት በ”ሞራል ክለሳ” ካራ እየሰለቡ፣ ትውልዱ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሸከም መገደዱ፣ አእምሮውን ለከፍተኛ ጭንቀትና ለተስፋ መቁረጥ ዳርጎታል።
ዛሬ በአውስትራሊያ የሚታየው ከፍተኛ የራስን ሕይወት ማጥፋትና የአእምሮ ጤና ቀውስ፣ የዚሁ ትውልዱን ማንነቱን፣ ትውፊቱን፣ እሴቱን እንዲጠላና እንዲጠየፍ የማድረግ ሸፍጥ ቀጥተኛ ውጤት ነው።
🚨 ወኔው የተሰለበ ትውልድ ለኑሮ የሚታጠቀው ድፍረት፣ ተሰፋ የሚያደርገውም የክብር ሕይወት ስለሚጠፋ፣ መጨረሻው ራሱን በራሱ ማጥፋት አልያም ለባርነት እጅ መስጠት ይኾናል።
ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ትርክት ማኅበራዊ “መካንነትን” ወልዷል። የአባወራነት መንፈሱና የኃላፊነት ወኔው የተነጠቀ ኦዚ፣ ለዘሩ ቀጣይነትና ለቤተሰቡ ጽናት የሚኾን መስዋዕትነት የመክፈል አቅሙን አጥቷል።
ተስፋ የቆረጠ ትውልድ በኦዚ ምድር የሰፈነው፣ ትምህርት ቤቱም ኑነ ቤተ ክርስቲያኑ ታሪኩን ኮንነው በማንነቱ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ ስላደረጉት ነው።
አርበኛ አውስትራሊያውያን ሀገርን ለማቅናት፣ ሥልጣኔን ለማስፋፋት የከፈሉትን መስዋዕትነት እንደ “ወንጀልና ጭቆና” በመቁጠር፣ ከጎላ መልካም በሥራቸውም ጥቂቷን ስሕተት በማራገብና በማድመቅ ትውልዱ በአባቶቹ፣ በታሪኩ እንዲያፍር ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ጫና ፈጥረዋል።
ይህ “የንስሐ” የሚመስል ነገር ግን አውራውን የማኮላሸት ትርክት ትውልዱን እንደ አንበሳ ደቦል ለንግሥና ለመሪነት ከማሳደግ ይልቅ፣ ሁልጊዜ አንገቱን ደፍቶ የሚኖርና ለሀገሩ ክብር ግድ የሌለው “የጥፋተኝነት እስረኛ” ባይተዋር ጃንደርባ አድርጎታል።
የአውስትራሊያ ቤተ ክርስቲያን ለዓለማዊው ፌሚኒዝም ርዕዮተ-ዓለም እጅ በመስጠቷ፣ ትውልዱ ስለ እውነትና ስለ ጽድቅ የሚሟገትበትን ድፍረት አጥቷል።
ቤተ ክርስቲያኒቱ ለጥቃትና ለግፍ “ዝምታን” እንደ ምርጥ ምግባር ስታስተምር፣ የወንዱን ድፍረት ወኔውን፣ ኃይል ጉልበቱን፣ ትጋት እልሁን፣ ቆራጥ አቋሙን ሁሉ “ከመርዛማ” ወንድነት መድባ ልጇቿን በእጆቿ ሰልባለች።
የወንድን የመሪነትና የኃላፊነት ሚና ከማጽናት ይልቅ፣ ለዘመናዊው የማኅበራዊ መዋቅር፣ ለኦዚ ቤተሰብ መፍረስ መንገዱን አመቻችታለች።
ቤተ ክርስቲያኒቱ የወንድን አርበኛዊና ቤተሰባዊ ወኔ ሰልባ አባወራነትንም ኮንና በማጥፋቷ፤ ትውልዱ ስለ ነገ፣ ስለ ትውልድ ተስፋ የሌለውና ለራሱ ክብር የማይሰጥ ኾኖ እንዲጠፋ እንዲመክን ተደርጓል።
0 Comments