ያለ እድሜ ያገረጅፋል መልክ ያጠፋል፣ ቁመና ያበላሻል/
ተወዳጆች ሆይ በቀን ሕዳር 20 በክፍል ሃያ አራት ስለ እልከኛው ዓይነ ጥላ በሰፊው ዓይተናል፡፡
በዚህ ክፍል ደግሞ ዓይነ ጥላ አካላዊ የሚታይ ውበትን የማጥፋት እና ሰውነትን የማገርጀፍ ተንኮሉን እንመለከታለን፡፡
ወዳጆቼ በአሁን ጊዜ መንግስት የዋጋ ግሽበት እንደሚለው የሰው ግሽበት እየተከሰተ ነው፡፡ ትላንት ያያችሁት ወጣት ዛሬ ግሽብ ብሎ፣ የወጣትነት ለግላጋ መልኩን ጥሎ፣ ያለ እድሜው ጉልምስናን አንጠልጥሎ ታዩታላችሁ፡፡ በእርግጥ ዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያ እየበላ የሚኖር ትውልድ እንኳን ያለ እድሜ መገርጀፍ፣ አርጅቶ ቢንጀፋጀፍ ላይደንቀን ይችላል፡፡ ግን ትንሹም ትልቁም ያለ እድሜው ሲገረጅፍ አንድ ስውር ነገር እንዳለ ግልጥ ነው፡፡ ያለ እድሜ የትልቅ ሰው ገጽታን ይዞ መታየት በህክምናው በዘር ትውልድ የሚተላለፍ ቢሆንም በእኛ ዘመን ግን የወጣት ጎላማሳ በዝቷል፡፡
በዚህ ክፍል በተለይ ምዕራባውያን የሚቸገሩበት እኛም አገር ያላቸው ሰዎች በፕሮቲን እና በፋት የበለጸጉ ምግብን ከመብላት እልፎ በማግበስበስ በሚመጣ ውፍረት ሳይሆን በመናፍስት ተንኮል የሚመጣን የሰውነት ውፍረት እና የውበት መጥፋትን እንመለከታለን፡፡
የዓይነ ጥላና ዛር መንፈስ ፊትን እና አካላትን ማገርጀፍ፣ ማወፈር እና ያረጀ ማስመሰል አንዱ ጠባያቸው ነው፡፡ እነዚህ ርኩሳን መናፍስት ያለ እድሜያችን በማገርጀፋቸው ብዙ ነገራችንን ለማበለሻት ይመቻቸዋል፡፡
በተለይ ዓይነ ጥላና ዛር በሰውነታችን ውስጥ ሲሰርጹ በውስጣችን ሆነው የውጪ ገጽታችንን ይቀይሩታል፡፡
ወዳጄቼ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውን አባቶችን ብትመለከቱ ከእድሜያቸው በላይ ሕፃን ይመስላሉ፡፡
የፊታቸው ወዝ የሚቀዳ ይመስላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሲዋሃዳቸው ፊታቸው ብሩህ ነው የሚሆነው፡፡ ከዚህ በተቃራኒ ያሉት ዓይነ ጥላና የዛር መንፈስ ዓላማቸው የእኛን ነገር ማሳጣት፣ ማበላሸት ስለሆነ በውስጣችን ሆነው የውጪ ገጽታችንን ይቀይሩታል፡፡
እስኪ አንድ የምታውቁትን ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡ የምታውቁት ሰው በፍጹም መጠጥ የማይጠጣና ስካርን የማይውቅ ሰው ይሆናል፡፡ ፊቱን ስታዩት ግን የሰካራም ፊት ይመስላል፡፡
እጅጉን ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ፊቱን ስታዩት እልም ያለ ነገረኛ ይመስላችኃል፡፡ አንዲትን ሴት ገና ዓይኗን ስታይዋት ነገር የሚናፍቃት ጠብ ጠብ የሚላት ይመስላችኃል፡፡ ተጫዋች የሆነ ሰውን ግንባሩን ስትመለከቱት ኮስታራ ፊት ያለው ይመስላችኃል፡፡ ወዘተ እነዚህ ነገሮች መናፍስቶች ከውስጥ ሆነው ማህበራዊ ሕይወታችንን ለማበለሻት የሚገለጡበት ተንኮል ነው፡፡ ስለዚህ በውስጥ ያለ ዓይነ ጥላና ዛር ያለ እድሜያችን ሊያወፍሩን ሊያገረጅፉን ይችላሉ፡፡
ውስጥ ተደብቆ አሸምቆ ያለ ዓይነ ጥላና ከቤተሰባችን በአንድም በሌላ የወረስነው የዛር መንፈስ በ19 ዓመታችን የሃያ ዘጠኝ ዓመት የፊት ገጽታ እንዲኖረን ያደርገናል፡፡ የሃያ አምስት ዓመት ወጣት ሴት የሠላሳ አምስት ዓመት፣ የሠላሳዋን የአርባ ዓመት እና ከዛም በላይ ሊያስመስላት ይችላል፡፡
ዓይነ ጥላና የዛር መንፈስ የፊት ገጽታችንን በማገርጀፍ፣ ሰውነታችንን በማወፈር ትልቅ ሰው በማስመሰል በጓደኞቻችን ዘንድ የመፈለግን ስሜት ሊያጠፋብን፣ የእጮኝነት እድልን ሊያሳጣን፣ የትዳር እድላችንን ሊዘጋብን ይችላል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ከውፍረት ጋር ለተያያዘ በሽታ ሊዳርገን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ለነርቭ፣ለወገብ ህመም/ዲስክ መንሸራተት/ ለተረከዝ ህመም፣ ለደም ግፊት፣ ለስኳር፣ ለልብ ድካም፣ ለተዘበራረቀ አተነፋፈስና ሰውነትን እንደ ልብ አለማዘዝ ከዛም በእነዚህ ችግሮች ለተስፋ መቁረጥና ለደብት
ይዳርገናል፡፡
በመንፈስ የመጣ የሰውነት ውፍረት ለማያውቅ ሰው በምቾት እና በድሎት የመጣ ይመስላቸዋል፡፡ አንዳንዶቹም ውፍረታቸው ለሰዎች ከምግብ ጋር የተያያዘ ሊመስላቸው ይችላል፡፡ ግን እነዚህን ሰዎች ቀረብ ብላችሁ ብትጠይቁ ምግብ እምብዛም ናቸው፡፡ አይበሉም ለማለትም እስኪያስደፍር ድረስ ምግብ ብዙም አይመገቡም፡፡
ዓይነ ጥላና የዛር መንፈስ በሁለት መልኩ ሊያወፍረን ይችላል፡፡ አንደኛው በልጅነታችን በመግባት መንፈሱ በውስጥ ተደላድሎ በመቀመጥ በከፍተኛ ሁኔታ ይወፍረናል፡፡
ሁለተኛው ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሔዋን ስንደርስ በሰዎች ዘንድ በመወደዳችን በመፈለጋችን በቅናት የሚገባው ዓይነ ጥላ ድንገት የሰውነት ለውጥ በማምጣት ያወፍረናል፡፡
ስንወፍር ደግሞ ውበታችን እስኪጠፋ፣ ሰውነታችን እንደ ባሎን እስኪነፋ ድረስ ነው የሚያወፍረን፡፡ የዛር መንፈስም ቢሆን ልክ እንደ ዓይነ ጥላው ውበታችንን እና የሰውነት ቅርጻችንን በማጥፋት ለድንገተኛ ውፍረት ይዳርገናል፡፡ እዚህ ላይ የምጨምርላችሁ በተለይ በመተት መድኃኒት የሚደረግባቸው ወይም በምግብ የተደገመበትን ነገር የበሉ ሰዎችም የውበት በመላሸት እና ድገተኛ ውፍረት ያጋጥማቸዋል፡፡ ያለወቁት እና ያልነቁት ደግሞ የወፈረውን ሰው አይተው ‹‹ፐ.. ወፈርሽ ተመችቶሻል፣ የሚገርም ነው ተስማምቶሃል›› እየተባሉ መንፈሱ ጥሩ ከለላ ያገኛል፡፡
ከምቾች እና ከድሎት ያልሆነ ግን ከዓይነ ጥላና ከዛር መንፈስ የሚመጣ ውፍረት የራሱ መገለጫዎች አሉት፡፡ ይህም የፊት ውበት መጥፋት፣ ፊት ላይ የማይጠፋ ብጉር መውጣት፣ ፊት ላይ የሚሻክር ነገር መውጣት፣ ብግ ብግ ያለ ነገሮች መውጣት፣ የዓይንና የፊት ማበጥ፣ ጠዋት ሲነሱ ፊት ያብጣል ቆይቶ ይቀንሳል፣ ፊት ላይ ክብድ ያለ ስሜት መሰማት፣ የፊት ቆዳ ቀለም መቀየር፣ መወየብ፣ መበለዝ፣ ዓመድ የተነፋበት መምሰል፣ ፊት እና ዓይንን መሳከክ፣ ዓይን ማልቀስ፣ መሞጭሞጭ እና ከዓይን አከባቢ ቆሻሻ መታየት፣ የዓይን ውበት መጥፋት፣ የዓይን ሽፋሽፍት መነቀል፣ ዓይን ማሳከክ፣ ቦጭቆ ጣል የሚል ስሜት መሰማት፣ ቅንድብና ሽፍሽፍት መርገፍ፣ ከንፈር መጥቆር እና ማረር ወዘተ ናቸው፡፡
ዓይነ ጥላና የዛር መንፈስ ሰውነትን ሲያወፍር መገለጫው ድንገተኛ የሰውነት መወፈር፣ የሰውነት ቅርጽ መጥፋት፣ ያልተለመደ የሰውነት ጠረን ማየት፣ ምቾት ማጣት፣ ሆድ አከባቢ ደርብርብ ቦርጭ መታየት፣ የሰውነት በተለይም ፊት፣ ወገብ፣ ሆድ፣ እጅና እግር አካባቢ ውፍረት ሳይሆን እብጠት መታየት፣ በውፍረቱ ሳብያ ሕመም መሰማት ወዘተ ናቸው፡፡
ብዙ ሴቶች መልክ ኖሯቸው በዓይነ ጥላና በዛር ምክንያት ፊታቸው በመገርጀፉና ሰውነታቸው በመወፈሩ ትልቅ ሰው በመምሰላቸው ለትዳር የሚጠይቃቸው ወንዶች በሥጋ ስሌት ውስጥ በመግባት ‹‹ትልቅ ናት፣ላትወልድ ትችላለች›› በማስባል የትዳር እድላቸውን ይዘጋል፡፡
ወዳጆቼ እኔም ለዚህ ምስክር በመሆን አንድ የማውቃት ልጅ በሃያ አምስት ዓመቷ ላያት ሰው ከ35-38 ዓመት የምትገመት ሴት ትመስላለች፡፡ ይቺ ልጅ ጸበል ሄዳ የያዛት የዛር መንፈስ የትዳር እድልዋን ለማበላሸት እንዳወፈራት ለፍልፎ ለቋታል፡፡ እነዚህ መናፈስቶች የሰውን ቁመናና ውብት ማጥፋት ብቻ ሳይሆን ያለ ጊዜያችን ጸጉራችንን በማሸበት ውጫዊ ገጽታችንን ይቀይራሉ፡፡
ዓይነ ጥላ እና የዛር መንፈስ ሰውነታችንን እንዴት ሊያወፍሩን ይችላሉ? ካልን መንፈሱ በሰውነታችን ውስጥ ከሥጋና ደማችን በመዋሃድ በውስታችን መርዙን ይሠራል፡፡
በሰውነታችን ውስጥ ያለው የመንፈሱ መርዝ ከተፈጥሮ ሰውነታችን ጋር ስለማይስማማ ሰውነታችን በሂደት እና በድንገት ሳናውቀው እያየነው መቆጣጠር በማንችለው መልኩ ማበጥ ይጀምራል፡፡ ወዳጆቼ ይህንን እብጠት ነው ውፍረት ብለን ስም የሰጠነው፡፡
በዓይነ ጥላና በዛር መንፈስ የሚመጣ የሰውነት እና የፊት እብጠት፣ የውበት መበላሸት ወይም ውፍረት ቀን ከሌሊት ስፖርት ብንሠራ፣ምግብ መብላት ብንቀንስ ሰውነታችን ላይቀንስ ይችላል፡፡
ተወዳጆች ሆይ ለዚህ መፍትሔው ምንድነው? ካልን የመጀመርያው ጸበል አብዝቶ መጠጣት ነው፡፡ በዚህም
የመንፈሱ መርዝ ከሰውነታችን በትውከት ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ ዝልግልግ እና አረፋ እየመሰለ ይወጣል፡፡ እንዲሁም በሽንት ይወጣል፡፡ ለዚህ ደግሞ ከ 2-5 ሌትር ጸበል እንዳቅም መጠጣትን ይጠይቃል፡፡ ሁለተኛው መስገድ ነው፡፡ በስግደት መንፈሱ ከሰውነታችን እየበነነ ሲሄድ ሰውነታችን ወደ ነበረበት ቦታ እየተመለሰ ይመጣል፡፡ ሦስተኛ በርትቶ በመጸለይ እና በመጠመቅ ዓይነ ጥላውና ዛሩ ከሕይወታችን ሲርቅ
የተበላሸብን ይስተካከላል፡፡ በተለይ ፊት እና ዓይን ላይ ተቀምጦ ውበትን ለሚያበላሸው ትክክለኛውን ቅብዓ ቅዱስ መቀባት አንዱ ትልቅ መፍትሔ ነው፡፡
ስለዚህ ይህ መናጢ ርኩስ መንፈስ ያለ እድሜያች እያገረጀፈ ውበታችንን፣ ቁመናችን፣ የትዳር እድላችንን እንዳያበላሽብን ልንነቃበት እና ልንዋጋው ይገባል፡፡
‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6
‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8
አንብበው ሲጨርሱ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያዳርሱ፡፡
0 Comments