ፓራካስ የራስ ቅሎች።

✍ እለ አጽበሐ | አዲስ ምልከታ

በዘመናችን መላው ዓለም ላይ ተድበስብሰው ከቀሩና በጥቂቶች ብቻ ከሚታወቁ ታሪኾች አንዱ የኔፍሊሞች ነው። የነርሱ ታሪክ ከጥንት ስልጣኔዎች ጋር እና፣ ከሚስጥር ማህበሮች ጋርም ያለው ቁርኝት ምንድን ነው፣ ታሪኩ ተድበስብሶ ለመቅረቱስ የነርሱ እጅ አለበት ወይ? የሚለው ይገኝበታል። በእርግጥ ታሪኩ ድብቅ መሆኑ ለነሱ ዓላማ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘም ሊሆን ይችላል፤ ያንን የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ። በዚህ ጽሑፍ ግን ያንን ወደ ጎን ትተን ተበታትኖ የሚገኘው ታሪክ ምንድነው? የሚለው ላይ እናተኩራለን።

በመጀመሪያ የኔፍሊም ታሪክ ከየት ነው የሚነሳው? በመጽሐፈ ሄኖክ እና በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በተለያየ ደረጃ የተጠቀሰ ቢሆንም ብዙዎች በማወቅም ሆነ በማወቅ ሀሰት እንደሆነ ለማሳየት ይጥራሉ።

ለምሳሌ በመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ውስጥ የሚገኘውን የቃየል ልጆች ታሪክ፣ በመጽሐፈ ሄኖክ ውስጥ ከሚገኘው የኔፍሊም ታሪክ ጋ የማምታታት ስህተት በብዙዎች ዘንድ ይታያል። ይህም ስህተት፣ በተለይ በኢትዮጵያ፣ ሰዎች የኔፍሊምን መኖር እስከመካድ አድርሷቸዋል። ይህን ስህተት ለማስተካከልና ትክክለኛውን የኔፍሊም ታሪክ ለመመልከትም ሲባል ሁለቱም ምን ይላሉ? የሚለውን እንይ።

በመጀመሪያ ትክክለኛው ታሪክ ምንድን ነው? የሚለውን ስናይ። የተወሰኑ መላእክት ከሰማይ ሆነው የሰውን ልጆች ኃጢአት አዩ፣ በዝሙት ወድቀው ሲስቱ ተመለከቱ። ወደ እግዚአብሔርም ቀርበው፦ እኛ እንደ አዳም መራቢያ የሆነውን አካል ብትሰጠን ኖሮ እንዲህ አንበድልም ነበር ብለው በትዕቢት ይናገራሉ። እግዚአብሔርም ይሁንላችሁ ብሎ ያንን ሥጋ አልብሶ ወደ ምድር ይልካቸዋል። ቁጥራቸውም 200 ሲሆን ከነሱም ውስጥ ስማዝያ (አለቃቸው)፣ አዛዝኤል፣ ራሚኤል ወዘተ ይገኙበታል። ወርደውም ኤርሞንኤም የሚባል ተራራ ላይ ያርፋሉ። ከዚያም የሰው ልጆች የሆኑትን ሴቶች ላለመገናኘት ቃል ይገባባሉ።

ነገር ግን ሴቶቹ ሲመጡ ቃላቸውን ሊጠብቁ አልቻሉም፣ ከነሱ ውስጥ ለየራሳቸው ሚስቶች አድርገው ይወስዳሉ። ከዚያም ወርደው ከሌሎቹ የሰው ልጆች ጋ ይቀላቀሉ፤ ለሰዎች ክፉ እውቅትንም ያስተምራሉ። ኮከብ ቆጠራ፣ ከእጽዋት ስሮች የተለያየ ነገር መስራት፣ የጦር መሳርያ አሰራር፣ የተለያዩ ራስን የማስዋብ ጥበቦች ወዘተ ያስተምራሉ። ከሴቶቹም ልጆችን ይወልዳሉ፣ ልጆቹም እጅግ ግዙፍ፣ አረመኔ፣ ሁሉንም ነገር የሰውን ልጅ ጨምሮ የሚበሉ፣ በኋላ ላይም የራሳቸውን ቤተሰቦች ወደ መብላት የዞሩ ናቸው።

ከዚያም መጽሐፉ እንደሚነግረን፣ ከኖህ ጥፋት በፊት ዓለምን በኃጢአት ያጥለቀለቀው አንዱ ምክንያት ይህ እንደሆነ ያሳያል። ከጥፋት ውሃው በፊትም ቅዱስ ገብርኤል ተልኮ በጦርነት እንዲጠፋፉ መቅሰፍትን እንዳወረደባቸው ይተርካል።

ይህ እንግዲህ የመጽሐፈ ሄኖክና በጥቂቱም የመጽሐፈ አክሲማሮስ ታሪክ ነው። መጽሐፈ ቀሌምጦስስ ምን ይላል? የሚለውን ስንመለከት፦

አዳምና ልጆቹ በሙሉ ደብር ቅዱስ የሚባል ተራራ ላይ ይኖሩ ነበር። ቃየንም ወንድሙ አቤልን ሲገድል ከዚያ ተባረረ፣ ወርዶም ከታች ባለው አከባቢ መኖር ጀመረ። ሚስትና ልጆችም ነበሩት፣ የርሱም ልጆች በተለያየ ኃጢአት የሚሰሩ ሆኑ። አቤል ከሞተም በኋላ በምትኩ የተወለደው ሴት ከልጆቹ ጋር በተራራው ላይ በቅድስና ህይወት ይኖሩ ነበር። በኋላም ከተራራው በታች የቃየል ልጆች በዝሙት በዘፈን ወዘተ እጅግ ትልቅ ኃጢአት ላይ ደረሱ። የዘፈኑ ድምጽም ላይ እስከ ተራራው ይሰማ ጀመር። ከዚያም የሴት ልጆች ጥቂቶቹ ወርደው ከቃየል ልጆች ጋር ቀጠሉ። በከፍተኛ ኃጢአትም ኖሩ። በኋላም ተራራው ላይ ያሉት ሁሉ እየወረዱ የኃጢአቱን ዓለም ተቀላቀሉ። የዓለም ኃጢአትም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ። ተራራው ላይ የቀሩትም ኖህ እና ቤተሰቦቹ ሆኑ። ከዚያም የጥፋት ውሃው መጣ።

እንግዲህ ሁለቱን ታሪኮች በዚህ ሁኔታ ካየን፣ ተመሳሳይ ናቸው ወይስ የተለያዩ? የሚለውን እንተንትን። ምን ያመሳስላቸዋል፣ ምንስ ያለያያቸዋል የሚለውን አንድ በአንድ እንይ።

ተመሳሳይነታቸው፦ በሁለቱም ታሪክ፣ ተራራ ላይ እና ታች የተለያዩ ነበሩ። ከላይ ያሉት ወርደው ታች ካሉት ጋራ ተቀላቀሉ። ከዚያም የዓለም ሃጢአት ከፍተኛ ደረጃ ደረሰ፣ የጥፋት ውሃም መጣ።

እሺ ልዩነታቸው ምንድን ነው?

- በመጀመሪያው ታሪክ፣ ተራራው ላይ የነበሩት መላእክት፣አዛዝኤል ስማዝያ ወዘተ ተብለው በስም የተጠቀሱ ናቸው። በሁለተኛው ደግሞ የአዳም ልጆችና የልጅ ልጆች፣ በትውልድ ቅብብሎሽ እስከ ኖህ ድረስ ያሉት ናቸው።

- በመጀመሪያው ታሪክ፣ ከተራራው በታች ያሉት የሰው ልጅ የሆኑ ሴቶች ናቸው። በሁለተኛው ደግሞ የቃየል ልጆች የሆኑ ሴቶችም ወንዶችም ናቸው።

- በመጀመሪያው ታሪክ፣ ተራራው ላይ ያሉት የሰው ልጅ ከታች ካሉት ከሆኑ ሴቶች ጋር ሲገናኙ፣ በሁለተኛው ደግሞ ተራራው ላይ ያሉት የሴት ልጆች ከታች ካሉት የቃየል ልጆች ጋር ተገናኙ።

- ማለትም፣ በመጀመሪያው ታሪክ፣ ሴት ልጆች የተባሉት ከተራራው በታች ነበሩ፣ በሁለተኛው ደግሞ የሴት ልጆች የተባሉት ከተራራው ላይ ነበሩ።

- በመጀመሪያው ታሪክ፣ "ሴት" የሚለው ሴት ፆታን ሲያመለክት፣ በሁለተኛው ደግሞ "ሴት" የሚለው በአቤል ምትክ የተወለደውን የአዳምን ልጅ ያመለክታል። በሌሎች ቋንቋዎች ለምሳሌ በኢንግሊዘኛ ብንመለከተው፣ የመጀመሪያው ሴት ልጆች የሚለው "women/girls/females" የሚለውን ሲይዝ፣ ሁለተኛው የአዳም ልጅ የሆነው ሴት ደግሞ "Seth" የሚለውን የሰው ስም/ስያሜ ይይዛል። ማለትም ታሪኮቹ በኢንግሊዝኛ ተጽፈው ቢሆን ኖሮ እንደዚያ ተለይቶ ይቀመጥ ነበር።

በአጠቃላይ፣ ሁለቱ ታሪኮች ተመሳሳይ ቢመስሉም፣ ያለምንም ጥርጣሬ ፍጹም የተለያዩ ታሪኮች መሆናቸውን ማሳየት እንችላለን። በዚህም ብዙ ሰዎች "ኔፍሊም የሚባሉ የሉም፣ መላእክት ከሰው ጋር አልተዋለዱም፣ የአዳም ልጅ ሴት እና የቃየል ልጆች ታሪክ ነው ብለው ራሳቸውም ሳይገባቸው የሚናገሩትን ትክክል እንዳልሆነ ማሳየት እንችላለን። በተጨማሪም፣ "መላእክት ከሰው ጋር አይዋለዱም፣ መዋለጃ አካል የላቸውም" ለሚለውም፣ በመጀመርያ፣ "እግዚአብሔር ምን ይሳነዋል? ይሆን ዘንድ ከፈቀደ አይሆንም ወይ??" እንላለን።

ተጨማሪ ለመመለስ ግን፣ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ላይ የሄኖክን ታሪክ ሲያብራራ፣ መላእክቱ እግዚአብሔርን "የነሱን ስጋ ብትሰጠን እንደነሱ አንስትም ነበር" ስላሉ ያንን ሰጋ እንደሰጣቸው ያስቀምጣል።

መጽሐፈ ሄኖክም መላእክቱን "ረዓይት"፣ ልጆቻቸውንም "ኔፍሊም" ብሎ በግልጽ አስቀምጧል። ተቃዋሚዎች ሰውን የሚያሳስቱበትን የቃየል-ሴት ታሪክ የሚተርከው መጽሐፈ ቀሌምንጦስ ደግሞ ስለ ረዓይትም ሆነ ስለ ኔፍሊም፣ ስለ ኤርሞንኤም ተራራ፣ ምንም አይናገርም። ይናገራል ያሉ ሰዎች ማስረጃውን አቅርበው መሞገት ይችላሉ። ነገር ግን አያገኙትም፣ እንደዚያ አይነት ማስረጃ የለምና።

ይህንን ጉዳይ በዚሁ ከገደልን፣ ወደ ቀጣዩ ወሳኝ ነገር እንለፍ። ለመሆኑ የኔፍሊሞች መጨረሻ ምን ሆነ? ስንል። መጽሐፈ ሄኖክ እንደሚነግረን፣ የነሱ ወላጆች የሆኑት ረዓይት በእግዚአብሔር ቅጣት እንደተካሄደባቸው፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ሚካኤል፣ ዑራኤል ተልከው ረዓይቱን ማንም በማይደርስባቸው ስውር ቦታዎች እስከ ዓለም ፍፃሜ እንዳሰሯቸው፣ ረዓይቱም ቅዱስ ሄኖክን ወደ እግዚአብሔር አማላጅነት ልከው ሄኖክ እግዚአብሔርን ሲለምንላቸው እንደነበር ይተርካል።

ልጆቻቸው ኔፍሊሞች ደግሞ፣ ከፊሎቹ በጦርነቱና በጥፋት ውሃው ሲሞቱ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ስጋቸው ተነስቶ፣ መንፈሳቸው ብቻ ቀርቶ የአየር ላይ አጋንንት ወደመሆን እንደተቀየሩ ያሳያል።

ነገር ግን ኔፍሊሞች ዝርያቸው ዛሬም ድረስ እንደተረፈ እንመለከታለን። አንዱ ትልቅ አመላካችም በመላው ዓለም እጅግ ግዙፍ ሰዎች፣ እስከ 3 ሜትር የሚሆኑ መኖራቸው ነው። ግን እንዴት ዛሬ ላይ ደረሱ? በኖህ የጥፋት ውሃ 8 ሰዎች ብቻ እንደተረፉ እናውቃለን። ኖህና ሚስቱ፣ ሶስቱ ልጆች እና ሚስቶቻቸው። በድምሩ ስምንት ሰው። እና የተለያዩ እንስሳት። ከዚያ ውጪ የተረፈ የለም። ታዲያ ኔፍሊሞች ከፊል ሰው ከሆኑ፣ እንዴት ሊተርፉ ቻሉ?

አንዱ መላ-ምት ሊሆን የሚችለው፣ ኔፍሊሞች ከሆነ ትውልድ በኋላ ከእንስሳት ጋርም ተቀላቅለው ይሆን? የሚለው ነው። ያም ዛሬ ላይ የሚስጥር ማህበሮች ዘንድ ተደብቀው ያሉት ሬፕታይል መሰል ሰዎች ከዚያ ተገኙ የሚል መልስ ይሰጠናል። ምን ያህል እውነት ነው? አናውቅም።

ሌላው መላ-ምት ደግሞ በያፌት ነገድ በኩል ተረፉ የሚል ነው። ይኸውም የያፌት ሚስት በከፊል የኔፍሊም ዝርያ አለባት የሚል መላምት ሲሆን፣ ታዲያ ያፌት እንዴት ኔፍሊም ሴትን ሊያገባ ቻለ? ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል። መልሱ ግን ቀላል ነው። ኔፍሊሞች በራሳቸው ከሰው ልጆች ጋር ተዋልደው ይሆናል። በሂደት በተዋለዱ ቁጥር ደግሞ ከሁለት እና ሶስት ትውልድ በኋላ ይበልጥ ወደ ሰው የቀረቡ ልጆች ይገኛሉ። የያፌት ሚስትም ከነሱ አንዷ ትሆናለች።

ያም ቢሆን የያፌት ሚስት መሆኗ አሳማኝ ነው ወይ? የካም ወይም የሴም ለምን አልሆነም? የሚለው ደግሞ ሌላ ወሳኝ ጥያቄ ነው። የዚህም መልሱ አይከብድም።

በመጀመሪያ መላእክቱ የሰውን አካል ሲወስዱ ሙሉ በሙሉ አይወስዱትም። ይልቁንም የራሳቸውን ጭምር ይይዛሉ። መላእክት እንደመሆናቸው ወርቃማ ፀጉር፣ እጅግ ነጭ የሚያበራ ፊት ኖሯቸው ይሆናል። ስለዚህ እነዚያ የመልካቸው መገለጫዎች በልጆቻቸው ላይም ይታያሉ። ያንን ስንመለከት ነጮች የተለዩ ገጽታዎች ያላቸው መሆኑ እውነትም የያፌት ዘሮች ያንን የወደቁት መላእክት ጂን በዘር መቀበላቸውን ያመለክተናል።

ወርዋማ ጸጉር እና ሰማያዊ ዐይን ያለው ሰው።
ቀይ ጸጉር ያላት ሴት፣ ጥቁር-ወርቃማ ጸጉር እና ቀይ ጺም ካለው ሰው ጋር።

ታዲያ ይህንን ሃሳባችንን የሚያጠናክርልን ነገር፣ እነዚህ ቀይ እና ወርቃማ ጸጉር፣ እንዲሁም ሰማያዊ እና አረንጓዴ ዐይን ያላቸው ሰዎች፣ ከዓለም ህዝብ አንጻር ብዛታቸው እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ ነው። እነዚህም በብዛት በአውሮፓ እና አሜሪካ የሚገኙ ሲሆኒ፣ በኤሺያ ደግሞ አልፎ አልፎ መካከለኛው ምስራቅ ውስጥ እና ክርሱም በስተ ሰሜን ካውካሰስ በሚባለው አርመንያ ያለችበት ቀጠና፣ እንዲሁም ቱርክ አከባቢ የሚገኙ ናቸው። ነገር ግን ከዓለም ህዝብ አንጻር እጅግ ዝቅተኛ ቁጥር ነው ያላቸው።

ወርቃማ ጸጉር ያላቸው ሰዎች ስብጥር።


ታድያ ይህንን ካልን፣ ወርቃማ እና ቀይ ጸጉር ያላቸው ህዝቦች ቁጥር ዝቅተኛ ከሆነ፣ እውነትም ያ ጂን የመጣው በከፊል ብቻ ጥቂት ህዝቦች ላይ፣ የያፌት ነገድ በሆኑት ነጮች በኩል ነው የሚለውን መረዳት እንችላለን። ከላይ በካርታው ላይ እንደምናየው የያፌት ነገዶች የሆኑ ህዝቦች በሙሉ ናቸው የሚታዩት፣ ቱርክን ጨምሮ።

ከዚህ በኋላ ታዲያ ልናነሳ የምንችለው አንድ ጥያቄ አለ። ያ የወደቁት መላእክት ጂን ሙሉ በሙሉ ነው የጠፋው፣ ወይስ ልክ እንደ ኔፍሊሞች ከተለመደው ሰው ወጣ ያለ ቁመት፣ መልክ ወዘተ ያላቸው ዛሬም አሉ? መልሱ የሚሆነው፣ አዎን አሉ ነው። የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊ እንደ አንድ መላምት ሊያነሳ የሚፈልገው ነገር፣ እነዚህ የወደቁት መላእክት ዝርያ ያላቸው ድቅሎች ዛሬም አሉ፣ ከሰውም የበለጠ ቁመት ብቻ ሳይሆን ረቂቅ አእምሮም ጭምር አላቸው፣ ብዙ የሚስጥር ማሕበራትም ከነዚህ ሰዎች ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የደም ትስስር አላቸው፣ ነገር ግን ገሃዱ ዓለም ላይ ላለመውጣት፣ በሚስጥር ተደብቀው ይኖራሉ የሚለው ነው።

ሌላም ጥያቄ መጠየቅ እንችላለን። ይህ ዝርያ በያፌት ነገዶች ወይም ነጮች ዘንድ ብቻ ቀረ ወይ? የሚለው ነው። ነገር ግን ያ እንዳልሆነ መረዳት እንችላለን። በኋላ ላይ የሴም፣ የካም አና የያፌት ነገዶች በተለያየ ጊዜ ተቀላቅለዋል። ስለዚህም ይህ ዝርያ በአንድም ሆነ በሌላ ሁኔት ተላልፏል። ለምሳሌ በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ የምናገኛቸው በዘፍጥረት ምዕራፍ ስድስት ውስጥ የሚገኙት፣ አልጋው 9 ክንድ በ 13 ክንድ የነበረው የባሳን ንጉስ፣ እንዲሁም የባቢሎንን ግንብ የገነባው ናምሩድ ተጠቃሽ ናቸው። በየዘመናቱም ቁመታቸው እጅግ ረጃጅም የሆኑ ሰዎች በመላው ዓለም ታይተዋል።

በዓለም ታሪክ ረጅም ተብለው የተመዘገቡ ሰዎች። በምስሉ በስተቀኝ ከታች በኩል ተፈጥሮአዊ ቁመት ያለው ሰው ይታያል።

ከዚህም በተጨማሪ፣ በታሪክ ትልቅ ቦታ ላይ ድርሰው ታዋቂነትና ዝና ሊያገኙ የቻሉ ሰዎች የዚህ ጂን እንዳለባቸው ይታያል። ይልቁንም፣ እንደ ነብዩ ሙሃመድ እና የሞንጎል ወራሪ የነበረው መላውን ኤሽያ የተቆጣረው ጄንጊስ ካን ቀይ ጸጉር ነበራቸው ይባላል። ሙሃመድ የኖረበት መካከለኛው ምስራቅ አከባቢ ያን አይነት የጸጉር ቀለም ያላቸው ሰዎች አንዳንዴ ይገኙ ነበር፣ ጄንጊስ ካንም መላውን አውሮፓ ተቆጣጥሮ የነበረ በመሆኑ እና ቀይ/ወርቃማ ጸጉር የነበራቸው ህዝቦች እርሱ የተወለደበት አከባቢ ይመጡ ስለነበር በነዚህ ምክንያቶች ሁለቱም ቀይ ጸጉር ካላቸው ሰዎች የመወለድ እድላቸው ጠባብ አይደለም። ምናልባትም በእስልምና የእምነቱ መሪዎች ቀይ ሂና ተቀብተው ጺማቸውን የሚያቀሉበት አንዱ ምክንያት ከዚያ ጋር የተያያዘ ይሆን?
በአፍጋኒስታን የሚኖር የእስልምና መሪ ጺሙን ቀይ ተቀብቶ።

በኢራቅ የሳዳም ሁሴን ምክትል የነበረው ሰው፣ በቀይ ጸጉሩ ይታወቅ ነበር።


ታድያ ጥቂት በታሪክ ካሉ ህዝቦች በተጨማሪ፣ ቀይ ጸጉር ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ በሙሉ የተለየ የአጽም ቅርጽ ያላቸው ሰዎች በብዛት የኖሩበት እና የራሳቸውን መንግስት መስርተው የገዙበት ጊዜ አለ። ይህም ከክርስቶስ ልደት 2 መቶ ዓመታት በፊት፣ በላቲን አሜሪካ፣ በሃገረ ፔሩ ነው። እነዚህም ሰዎች "ፓራካስ" የሚባሉ ናቸው። እጅግ አስደናቂ ታሪክም አላቸው።
የፓራካስ የራስ ቅሎች፣ ከቀይ ጸጉራቸው ጋር።.