ወሀቢያ ምንድን ነው ? ከየት መጣ?


ወሀቢያ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሐመድ ኢብን አብደል ዋሂብ /1703-1792 ዓ.ም./ በተባለ ሰው የተመሠረተ የእስልምና ርእዮተ ዓለም ነው። ኢብን አብደል ዋሂብ ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የብዙ እስላሞችን ቀልብ የሳበውን አዲሱን አክራሪ እስልምና መሠረት የጣለ ነው። ተከታዮቹ ራሳቸውን ዋሂዲኖች ብለው ይጠራሉ። ትርጉሙም “በተውሂድ የሚያምኑ” ማለት ነው።

መሐመድ ኢብን አብደል ዋሂብ የተወለደው በማዕከላዊው ዐረቢያ ከሪያድ በስተ ስሜን ዑያናህ በተባለ ሥፍራ ከሃንባሊ የእስልምና ት/ቤት ጋር ግኑኝነት ከነበራቸው ቤተሰቦች ነው። አብዛኞቹ ቤተዘመዶች ከዚህ ት/ቤት የወጡ መምህራን ናቸው። በልጅነቱ በወግ አጥባቂው የሱኒ እስልምና ትምህርት ተኮትኩቶ አደገ፡ ከዚያም ለበለጠ ዕውቀት ወደ መካ እና መዲና ተጓዘ። በሃራማየን ት/ቤት በዘመኑ ዋና የአክራሪ እስልምና አቀንቃኞች ከነበሩት ከመሐመድ ሐያት አል ሲንዲ ከፍተኛ ዕውቀት አግኝቷል። በዚያም በተለይም ሃዲትን በተመለከተ በቂ የሆነ ዕውቀት ለመጨበጥ ችሏል። አብደል ዋሂብ በሃዲት በተገለጠው የጥንቱ እስልምና አሁን በሚያየው እስልምና መካከል ያለው ልዩነት ያሳስበው ነበር።
በልዩ ልዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ዕውቀቱን ካጎለመሰ በኋላ ወደ ሀገሩ ወደ ናጅድ ከተማ ተመለሰ። በዚያም ሕዝቡ የያዘውን የተለመደ ዓይነት እስልምና በመተው ቃል በቃል ቁራዓንን በሱኒ የእስልምና መርህ መሠረት እንዲከተል ማስተማር ጀመረ። ምንም እንኳን መጀመርያ ላይ ብዙዎች ቢቃወሙትም የዳሪያው ገዥ ሙሀመድ ኢብን ሳዑድ ጥሪውን በመቀበል የሃሳቡ ደጋፊ ሆነ። በአክራሪው የእስልምና መምህርና በጦረኛው መሪ መካከል የተጀመረው ወዳጅነት ወታደራዊ የሆነ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት በቃ። ይህ እስላማዊ ወታደራዊ መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዛቱን ወደ ሌላው የዐረቢያ ልሳነ ምድር ማስፋፋት ቻለ።
ይህ ኃይል በ1802 ዓ.ም. በደቡብ ኢራቅ የነበሩትን የሺአቶች ቦታዎች አስለቀቀ፡ በ1803 ዓ.ም. ደግሞ መካን ተቆጣጠረ። በዚያም የመጀመርያው ጠንካራ የሳዑዲ መንግሥት ተመሠረተ። በወቅቱ የእስልምናውን ዓለም አንድ አድርገን እንገዛለን ብለው የተነሱት ኦቶማን ቱርኮች ሁኔታው ስላሰጋቸው በግብጽ የነበረውን ጦር ወደ ሳዑዲ ላኩት። በዚህ ምዕራባዊውን አሠራር ይዞ የነበረው የኦቶማን ቱርክና አዲስ በመነሳሳት ላይ በነበረው ዐረባዊው አክራሪነት መካከል በተደረገው ጦርነት የሳዑዲ ወሀቢያዎች ለጊዜው ተሸነፉ። በ1818 ዓ.ም. የመጀመሪያው የሳዑዲ መንግሥት ተጠናቀቀ።

ወሀቢዝም ማናቸውንም ዓይነት የሱፊ እስልምና አካሄዶችን አይቀበልም። የተቀደሱ ሰዎች የሚባል ነገርን አያውቅም፡ በዚህ ዓይነት አምልኮ የተስፋፉ ስዎችም ከእስልምና ያፈነገጡ በመሆናቸው ሞት ይገባቸዋል ይላል። ከቁርዓንና ከሱና በስተቀር ሌላ የእስልምና መጽሐፍ አይቀበልም። እስልምና ብቸኛ የድኅነት መንገድ ነው ይህንን ደግሞ ሰዎች በውድም ሆነ በግድ መቀበል አለባቸው፡ ስለዚህም የተቀደሰ ጦርነትን ማካሄድ አስፈላጊ ነው ይላል። /ሱረቱ 8:65/

ይህ የወሀቢዝም አስተሳሰብ በሶማልያ ከሚገኘው የአልሸባብ ቡድን እስከ አል ቃኢዳ ድረስ ያሉ የዘመናችን አሸባሪዎች የሚመሩበት አስተሳሰብ ነው። የሀገራችን እና የቤተ ክርስቲያናችን የዘመኑ ፈተናም ይህ ነው። ወሃቢዝም በየሀገሩ በተለያየ ስም ይጠራ እንጂ አሠራሩ ተመሳሳይ ነው፡ እስልምናን አክራሪ በሆነ መንገድ ኃይል ቀላቅሎ መጠቀም ነው። የወሀቢዝም መነሻም መስፋፊያውም ሳዑዲ ዐረቢያ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ዋናው ድጋፍ የሚገኘው ከሳዑዲ ነው።

የ20 መክዘ የወሀቢያ መስፋፋት

1. የመንግሥት መመስረት (1932)

ዘመናዊ ሳዑዲ አረቢያ በIbn Saud ተመሠረተ። ከዚህ በኋላ ወሀቢዝም የመንግሥት ዋና ሀይማኖታዊ መርህ ሆነ። ይህ ማለት፦

✍የእምነት ትምህርት በመንግሥት ቁጥጥር ውስጥ ገባ
✍የእስልምናተቋማት በመንግሥት ድጋፍ ተጠናከሩ
✍የወሀቢ ትምህርት በአገር ውስጥ ተስፋፋ

2. የነዳጅ ድፍድፍ  (1970ኛው ዘመን)

1970ኛው ዘመን የነዳጅ ዋጋ  እየጨመረ ሲሄድ ሳዑዲ አረቢያ እጅግ ታላቅ ገቢ አገኘች። ይህ ገቢ የወሀቢ አስተሳሰብን ዓለም አቀፍ ለማስፋፋት ተጠቃሚ ሆነ።

በዚህ ምክንያት፦

✍በአፍሪካ፣ እስያ እና አውሮፓ መስጂዶች ተገነቡ
✍ኢስላማዊ ማዕከላት እና ትምህርት ቤቶች ተመሠረቱ
✍ወሀቢዝምን የሚያቀነቅኑ መጽሐፍት ታተሙ ወደ ተለያዩ  ቋንቋዎች ተተረጎሙ
✍ለውጭ ተማሪዎች የትምህርት እድል (Scholarship) መስጠት።

3. የትምህርትና  ተቋማት መስፋፋት

Islamic University of Medina
Muslim World League

እነዚህ ተቋማት ከዓለም አቀፍ ተማሪዎችን በመቀበል የወሀቢያን አስተሳሰብ

ይዘው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አደረጉ።

4. አፍጋኒስታን ጦርነት (1979–1989)

በ1979 ሶቪየት ሀገር አፍጋኒስታንን በወረረች ጊዜ፣ ሳዑዲ አረቢያ ከአሜሪካ ጋር በመተባበር የሙጃሂዲን ኀይሎችን ደገፈች።

ይህ ሁኔታ፦

የጂሃድ አስተሳሰብ እንዲስፋፋ አደረገ፣ ዓለም አቀፍ እስላማዊ ኔትዎርኮች እንዲፈጠሩ በር ከፈተ።

Post a Comment

0 Comments